ኢትዮጵያ በሁለተኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርአንና አዛን ውደድር ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች

ኢትዮጵያ በሁለተኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርአንና አዛን ውደድር ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ያስተናገደችው የ2017 ዓለም አቀፍ የቁርአንና አዛን ውድድር እሁድ እለት ተጠናቋል። በፍጻሜው ኢትዮጵያ በሴቶች የቁርአን ሂፍዝ እንዲሁም በወንዶች አዛን ዘርፍ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች። በውድድሩ በወንዶች ቁርአን ሂፍዝ ሊቢያ፣ በወንዶች አዛን ኢንዶኔዢያ፣ በቁርአን ሂፍዝ ሴቶች የመን እንዲሁም በወንዶች ቁርአን ቲላዋ (ድምጽ ማውጣት) ግብጽ አንደኛ በመውጣት አጠናቀዋል። በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነትና በዘይድ ኢብን ሳቢት የቁርዓን ማኅበር አማካኝነት በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የቁርአንና አዛን ውድድር ላይ 60 ሀገራት ተሳትፈው እንደነበር መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ከማህበራዊ ትሥሥር ገጾች የተገኙ ምስሎች መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik