የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ እና በሩሲያ ፌድሬሽን ምክርቤት  የአለም አቀፍ ጉዳዩች ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አንድሬይ ክሊሞቭ  ተወያዩ

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ እና በሩሲያ ፌድሬሽን ምክርቤት የአለም አቀፍ ጉዳዩች ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አንድሬይ ክሊሞቭ ተወያዩ በዉይይታቸው ወቅት ፤ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ማእረግ የዲሞክራሲ ማስተባበሪያ ማእከል ሀላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እንደተናገሩት፦ ኢትዩጵያ በአረንጓዴ ልማት ፣ በግብርና ፣ በኢንፎርሜሽን እና ኮሚኒኬሽን ፣ በኢንዱስትሪ እና ሌሎችም ዘርፎች ላይ ስኬታማ ጉዞ እና ፈጣን እድገት እያስመዘገበች ነው ብለዋል። የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ ፤ ኢትዩጵያን በዲፕሎማሲ ዘርፍ ከብዙ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት እንድታጠነክር እድል ሰጥቷታል በማለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የሩሲያው ባለስልጣን በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራቱ የቆየ እና ጠንካራ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰዉ ፤ በብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ላይ በመጋበዛቸዉ የላቀ ምስጋናቸውን እና አክብሮታቸውን እናቀርባለን ብለዋል። ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በንግድ ፣ በኢንቨስትመንት ፣ በግብርና እና በሌሎችም ዘርፍ ያላቸውን ትብብር አጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ክሊሞቭ አረጋግጠዋል በማለት ሚዲያዎች ዘግበዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik
የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ እና በሩሲያ ፌድሬሽን ምክርቤት  የአለም አቀፍ ጉዳዩች ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አንድሬይ ክሊሞቭ  ተወያዩ በውይይታቸው ወቅት፤ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ማእረግ የዲሞክራሲ ማስተባበሪያ ማእከል ሀላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት፣ በግብርና፣ በኢንፎርሜሽን እና ኮሚኒኬሽን፣ በኢንዱስትሪ እና ሌሎችም ዘርፎች ስኬታማ ጉዞ እና ፈጣን እድገት እያስመዘገበች ነው ብለዋል። የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲ ዘርፍ ከብዙ ሀገራት ጋር  ያላትን ግንኙነት እንድታጠነክር እድል ሰጥቷታል ሲሉም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የሩሲያው ባለስልጣን በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራቱ የቆየ እና ጠንካራ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰዉ ፤ በብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ላይ በመጋበዛቸዉ የላቀ ምስጋናቸውን እና አክብሮታቸውን አቅርዋል። ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በግብርና እና በሌሎችም ዘርፍ ያላቸውን ትብብር አጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ክሊሞቭ አረጋግጠዋል ሲሉ ሚዲያዎች ዘግበዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia