ኢትዮጵያ የብሪክስን አጋርነት ከአባል ሀገራቱ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ትጠቀምበታለች ተባለ

ኢትዩጵያ የብሪክስን አጋርነት ከአባል ሀገራቱ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ትጠቀምበታለች ተባለበኢትዩጵያ የብሪክስ አጋርነት ነባር ባለሙያዎች ቴክኒካል ኮሚቴ ፤ በጎርጎሮሳዊያኑ 2025 በብራዚል ፕሬዝዳንትነት ወቅት የሚኖራትን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በትላንት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስብሰባ አካሂዷል። ስብሰባውን የመሩት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ ልዩ የፖሊሲ አማካሪ የሆኑት አምባሳደር ሚኒሊክ አለሙ ጌታነህ ናቸው። በስብሰባው ወቅት ፤ በጎርጎሮሳዊያኑ 2024 ኢትዩጵያ በብሪክስ ውስጥ የነበራትን እንቅስቃሴ እና ያሳካቻቸውን ተግባራት እና ለ2025 የያዘችውን እቅድ አስመልክቶ ፤ የአለም አቀፍ ድርጅቶች ጉዳዩች ዳይሬክተር ጀነራል እና የኢትዩጵያን የብሪክስ እንቅስቀሴ በሀላፊነት የሚመሩት አምባሳደር ለምለም ፍስሀ ማጠቃላይ ሰጥተዋል።አምባሳደሯ እንዳስታወቁት ኢትዩጵያ የብሪክስ አጋርነት ያላትን ትብብሮች የምታሳድግበት ፣ ብሄራዊ ጥቅሟን የምታስከብርበት እና የውጭ ፖሊሲዋን አላማዎች የምታስፈፅመበት ተጨማሪ መድረክ ነው። ጨምራም ኢትዩጵያ ፤ የብሪክስን አጋርነት ፦ በግብርና ፣ መሰረተ ልማትን በማሳደግ ፣ በጤና ፣ በትምህርት ፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ፤ ከአባል ሀገራቱ ጋር ያላትን የሁለትዩሽ ግንኙነቶች ተጨባጭ በሆነ እና የጋራ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ በተሻለ መንገድ እየተጠቀመችበት መሆኑን አስረድተዋል።በውይይቱ 21 የመንግስት ተቋማትን የወከሉ ባለሙያዎች መሳተፋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik
ኢትዮጵያ የብሪክስን አጋርነት ከአባል ሀገራቱ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ትጠቀምበታለች ተባለየኢትዮጵያ የብሪክስ አጋርነት የባለሙያዎች ቴክኒካል ኮሚቴ በ2025 የብራዚል ሊቀመንበርነት ዘመን ሀገሪቱ የሚኖራትን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ትላንት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስብሰባ አካሂዷል። ስብሰባውን የመሩት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዩ የፖሊሲ አማካሪ የሆኑት አምባሳደር ሚኒሊክ አለሙ ጌታነህ ናቸው። በስብሰባው ወቅት በ2024 ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ የነበራትን እንቅስቃሴ እና ያሳካቻቸውን ተግባራት እንዲሁም ለ2025 የያዘችውን እቅድ አስመልክቶ የአለም አቀፍ ድርጅት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል እና የኢትዮጵያን የብሪክስ እንቅስቀሴ በሀላፊነት የሚመሩት አምባሳደር ለምለም ፍስሀ ማጠቃላይ ሰጥተዋል።አምባሳደሯ እንዳሉት ብሪክስ ለኢትዮጵያ የአጋርነት ትብብሮቿን የምታሳድግበት፣ ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስከብርበት እና የውጭ ፖሊሲ አላማዎቿን የምታስፈፅመበት ተጨማሪ መድረክ ነው። አክለውም ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ግብርና፣ መሰረተ ልማት፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ከአባል ሀገራቱ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ተጨባጭ በሆነ እና የጋራ ጥቅምን ባስጠበቀ መልኩ በተሻለ መንገድ እየተጠቀመችበት መሆኑን አስረድተዋል።በውይይቱ 21 የመንግስት ተቋማትን የወከሉ ባለሙያዎች መሳተፋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia