የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፤ በሀገራቸው ያለውን ሁከት አስመልክቶ የአለም አቀፍ ኤጀንሲዎችን ዝምታ  አወገዙ

የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፤ በሀገራቸው ያለውን ሁከት አስመልክቶ የአለም አቀፍ ኤጀንሲዎችን ዝምታ አወገዙ " በኪጋሊ አገዛዝ እና ደጋፊዎቹ አማካኝነት በግዛታችን ውስጥ የሚፈፀመውን ግፍ እያያቹ ምንም አለማድረጋቹ እና በዝምታ ማለፋቹን ስድብ የሚሆነው ለኮንጎ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሰላም እና ፍትህን ዋጋ ለሚሰጡት የሰው ልጆች በሙሉ ነው" በማለት ፍሌክስ ቺሴኬዲ ለህዝባቸው ንግግር አድርገዋል። ፕሬዚዳንቱ ፤ በኮንጎ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ወረራ አስመልክቶ የአለም አቀፍ ድርጅቶች ዝምታ "ችግር ያለባቸውን ድንበሮች" በራሳቸው መንገድ መልሰው እንዲዋጉ ያደርጋቸዋል በማለት ተናግረዋል። ቺሴኬዲ "የሩዋንዳውን አረመኔያዊ ጥቃት" ሲሉ የጠሩትን ድርጊት ለመቃወም ሀገሪቱ አንድ እንድትሆን ጥሪ አቅርበዋል።ፕሬዝዳንቱ በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል የምተገኘውን የጎማ ከተማን ፤ በሩዋንዳ ጦር ድጋፍ በኤም 23 አማፂያን መያዝ አውግዘዉ ፤ የሩዋንዳ ጦር በኮንጎ ግዛት ውስጥ መገኘት "የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ቻርተር የሚጥስ" ተግባር ነው በማለት ኮንነዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik