የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

የአለም ባንክ ኢትዮጵያ እያደረገች ላለችው የማክሮኢኮኖሚ ለውጦች ያለውን ድጋፍ በትጋት እንደሚቀጥለበት አስታወቀ የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በአለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር አና ቤርዴ እና በምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና ምክትል ፕሬዚዳንት ቪክቶሪያ ኩዋዋ ከተመራ ልዑካን ቡድን ጋር በኢትዮጵያ የልማት ትብብር ጉዳይ ላይ ተወያዩ። አቶ አህመድ ሺዴ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ታንዛኒያ ውስጥ የተካሄደው የሚሽን 300 የአፍሪካ የኃይል ጉባዔ በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ የዓለም ባንክን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።ባንኩ ከሌሎች የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በአፍሪካ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት የሌለውን የህዝብ ቁጥር በጎርጎሮሳውያኑ 2030 በ50 በመቶ ለመቀነስ ተልዕኮ 300 ላይ እየሰራ መሆኑን እና ይህም በአህጉሪቱ ለሚገኙ 300 ሚሊዮን ሰዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ማለሙ ተዘግቧል።በአሁኑ ባንኩ ወቅት ከ17 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚገመት ኢንቨስትመንት በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ ይገኛል።ቢርዴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚና የፋይናንስ ዘርፍ ማሻሻያዎችን በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረጓን እና እስካሁን ድረስ ያገኘችውን ውጤት አድንቀዋል። የዓለም ባንክ እነዚህን ጅማሬዎች ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነትም በድጋሚ አረጋግጠዋል።ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ የግሉ ዘርፍ ፍላጎቶችን ለማሟላት ማሻሻያዎችን ማስፋት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።ሁለቱም ወገኖች ወደፊት ለመራመድ ጠንካራና ቀጣይነት ያለው ትብብርና አጋርነት አስፈላጊነት ላይ መስማማታቸውን ተገልጿል በማለት ሚዲያዎች ዘግበዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopiaፀ
Sputnik
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ በዓለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር አና ቤርዴ እና በምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና ምክትል ፕሬዚዳንት ቪክቶሪያ ኩዋዋ ከተመራ ልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል። ሚኒስትሩ ባንኩ በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ዘርፎች ከ17 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የኢንቨስትመንት መጠን እንዳለው አመልክተዋል። ለዓለም ባንክ የስራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያን ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም አስመልክቶ መረጃ የሰጡት ሚኒስትሩ፤ መንግስት በሪፎርሙ አማካኝነት በታክስ እና የፋይናንስ ዘርፍ ማሻሻያ በማድረግ ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። በቀጣይም ይህን ጥረት አጠናክሮ ለመቀጠል ቁርጠኝነት እንዳለ አረጋግጠዋል። ቢርዴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚና የፋይናንስ ዘርፍ ማሻሻያዎችን በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረጓን እና እስካሁን ድረስ ያገኘችውን ውጤት አድንቀዋል። የዓለም ባንክ ማሻሻያውን ለመደገፍ ቁርጠኛ እንደሆነም በድጋሚ አረጋግጠዋል። ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ ለግሉ ዘርፍ ፍላጎቶች ምላሽ የሚሰጡ ተጨማሪ ማሻሻያዎችን ማድረግ እንደሚያስፈልግም አንስተዋል። በውይይቱ ኢትዮጵያ እና ዓለም ባንክ ትብብር እና አጋርነታቸውን ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopiaፀ