ፕሬዚዳንት ካጋሜ አስፈላጊ ከሆነ ሩዋንዳ ደቡብ አፍሪካን ለመግጠም ዝግጁ መሆኗን አስታወቁ

ፕሬዚዳንት ካጋሜ አስፈላጊ ከሆነ ሩዋንዳ ደቡብ አፍሪካን ለመግጠም ዝግጁ መሆኗን አስታወቁየሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በቅርቡ በመገናኛ ብዙሃንን መረጃዎችን "አዛብተዋል" በማለት እንዲሁም በምስራቅ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ ያለውን ሁኔታና ኤም 23 አማፂ ቡድን በሩዋንዳ እንደሚገደፍ መገለጹን እና ቡድኑ ይዞታውን እያስፋፋ መሄዱን አስመልክተው የሩዋንዳን አቋም ግልጽ አድርገዋል።የሩዋንዳ መከላከያ ሰራዊት ፕሮፌሽናል ሰራዊት እንጂ ሚሊሺያ አለመሆኑን አፅንዖት ሰጥተው ፤ በኮንጎ የሰላም ተልእኮ ውስጥ ያሉት የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች የሰላም ጥረቶችን የሚያሳንሱ ጸባጫሪ ኃይል ናቸው ሲሉ ተችተዋል።ካጋሜ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ የሰጡትን ማስጠንቀቂያዎች በመቃወም ከሠላማዊ መፍትሄዎች ይልቅ ግጭትን ከመረጡ ሩዋንዳ ደቡብ አፍሪካን ለመግጠም ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል። "ደቡብ አፍሪካ ግጭትን የምትመርጥ ከሆነ ሩዋንዳ በጉዳዩ ላይ በማንኛውም ቀን ለመጋፈጥ ዝግጁ ናት " ሲሉ ካጋሜ በኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።ይህ የሆነው ራማፎሳ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ለሞቱት 13 የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች የኤም 23 አማፂያን እና የሩዋንዳ መከላከያ ሰራዊትን ወቅሰዋል መባሉን ተከትሎ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik
ፕሬዚዳንት ካጋሜ አስፈላጊ ከሆነ ሩዋንዳ ደቡብ አፍሪካን ለመግጠም ዝግጁ መሆኗን አስታወቁየሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ በሩዋንዳ ይደገፋሉ የሚባሉት የኤም23 አማፂ ቡድን በምሥራቅ ኮንጎ የሚያደርጉትን ግስጋሴ በተመለከተ የሩዋንዳን አቋም እና "የተዛባ" ነው ባሉት የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ዙርያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የሩዋንዳ መከላከያ ሰራዊት ፕሮፌሽናል ጦር እንጂ ሚሊሻ እንዳልሆነ አፅንኦት ሰጥተው፤ በኮንጎ የሚገኘው የደቡብ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ ተልዕኮ የሰላም ጥረትን የሚያደናቅፍ ጠብ አጫሪ ሃይል ነው ሲሉ ተችተዋል። ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ውድቅ ያደረጉት ካጋሜ፤ ደቡብ አፍሪካ ከሰላማዊ መፍትሄ ይልቅ ግጭትን የምትመርጥ ከሆነ ሩዋንዳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነች ብለዋል። "ደቡብ አፍሪካ ግጭትን የምትመርጥ ከሆነ ሩዋንዳ ተመጣጣኝ ምላሽ ትሰጣለች" ሲሉ ካጋሜ በኤክስ የትስስር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል። የካጋሚ ምላሽ ራማፎሳ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ለሞቱት 13 የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች የኤም23 አማፂያን እና የሩዋንዳ መከላከያ ሃይሎች ተጠያቂ ናቸው ማለታቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia