የአፍሪካ ህብረት በኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ የሚንቀሳቀሰው ኤም23 አማጺ ትጥቅ እንዲፈታ እና ወደ ውይይት እንዲገባ ጥሪ አቀረበ

የአፍሪካ ህብረት በኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ የሚንቀሳቀሰው ኤም23 አማጺ ትጥቅ እንዲያስቀምጥ እና ወደ ውይይት እንዲገባ ጥሪ አቀረበሰኞ ዕለት የኤም 23 ንቅናቄ አባላትን የሚያካትተው አማፂያን ጥምረት በምስራቅ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ ትልቅ ከተማ የሆነችውን የሰሜን ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ የሆነችውን ጎማን መያዙን ተናግሯል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ሩዋንዳ ወታደሮቿን ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንድታስወጣ ጥሪ አቅርበዋል። " የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና የፀጥታ ኮሚሽነር የሆኑት ባንኮሌ አዶዬ ፤ በኤም 23 እና በሌሎችም አሉታዊ ኃይሎች የተፈጸመውን ጥቃት አውግዘው የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና የግዛት አንድነት ሙሉ በሙሉ እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል። ኤም 23 የጦር መሳሪያውን እንዲያስቀምጥ፣ በጎርጎሮሳውያኑ ነሃሴ 2024 የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነትን እንዲያከብር እና ለሰላማዊ መፍትሄ ቅድሚያ እንዲሰጥ አሳስበዋል" ሲል የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የፖለቲካ ጉዳዮች ዲፓርትመንት ማክሰኞ ዕለት በኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል።.አዶዬ አክለውም የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ባለሥልጣናትን ለመደገፍ እና በተቃዋሚ ወገኖች መካከል ውይይት ለማሳከት የናይሮቢ የሰላም ኢኒሺየቲቭ በማዕቀፍ ሥራውን እንደገና እንዲጀመር ጠይቀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik
የአፍሪካ ህብረት በኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ የሚንቀሳቀሰው ኤም23 አማጺ ትጥቅ እንዲፈታ እና ወደ ውይይት እንዲገባ ጥሪ አቀረበሰኞ ዕለት የኤም23 ንቅናቄ አባላትን የሚያካትተው የአማፂያን ጥምረት በምስራቅ ኮንጎ ትልቋን ከተማና የሰሜን ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ የሆነችውን ጎማን መያዙን ተናግሯል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ሩዋንዳ ወታደሮቿን ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እንድታስወጣ ጥሪ አቅርበዋል። "የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና የፀጥታ ኮሚሽነር ባንኮሌ አዶዬ፤ በኤም 23 እና በሌሎችም አሉታዊ ኃይሎች የተፈጸመውን ጥቃት አውግዘው የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና የግዛት አንድነት ሙሉ በሙሉ እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል። ኤም 23 የጦር መሳሪያውን እንዲያስቀምጥ፣ በጎርጎሮሳውያኑ ነሃሴ 2024 የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያከብር እና ለሰላማዊ መፍትሄ ቅድሚያ እንዲሰጥ አሳስበዋል" ሲል የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የፖለቲካ ጉዳዮች ዲፓርትመንት ማክሰኞ ዕለት በኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል።አዶዬ አክለውም የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባለሥልጣናትን ለመደገፍ እና በተቃዋሚ ወገኖች መካከል ውይይት ለማሳከት የናይሮቢ የሰላም ኢኒሺየቲቭ ሥራውን እንደገና እንዲጀመር ጠይቀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia