የናይጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፕሬዝዳንት ቲኒቡን ተደጋጋሚ የውጭ ጉዞ ተከላከሉ

የናይጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፕሬዝዳንት ቲኒቡን ተደጋጋሚ የውጭ ጉዞ ተከላከሉ ሚኒስትሩ ዩሱፍ ቱጋር ቲኒቡ የሚያደርጓቸው ተደጋጋሚ ጉዞዎች ዓለም አቀፍ ግኑኝነቶችን ለማጎልበት እና የኢንቨስትመንት ስምምነቶችን ለማሳከት ወሳኝ ናቸው ሲሉ ተከላክለዋል። በቻናል ቴሌቪዥን ፖለቲክስ ቱዴይ ላይ ቀርበው ባደረጉት ገለጻ የጉዞዎቹን ጠቀሜታ ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ቲኒቡ በብራዚል ባደረጉት ጉብኝት 2 ቢልዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ማግኘታቸውን ተናግረዋል። አዲስ መሪ እንደመሆናቸው መጠን ግኑኝነቶችን ለማጠናከር እና እድሎችን ለመሳብ፤ ከዓለም መሪዎች ጋር መገናኘት አለባቸው ሲሉም ተከራክረዋል። የጉዞ ወጪን በተመለከተ የሚቀርቡ ስጋቶችን ውድቅ ያደረጉት ዩሱፍ ቱጋር፤ ከወጪው ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ እንደሚበልጥ አጽንኦት ሰጥተዋል። "ብዙ እየተጓዝን አይደለም። የተሻለ መስራት አለብን" ብለዋል ቱጋር። አ.አ.አ 2023 ወደ ሥልጣን የመጡት ቲኑቡ፤ 32 ጉዞዎችን አድርገው 19 ሀገራትን ጎብኝተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik
የናይጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፕሬዝዳንት ቲኒቡን ተደጋጋሚ የውጭ ጉዞ ተከላከሉ ሚኒስትሩ ዩሱፍ ቱጋር፤ ቲኒቡ የሚያደርጓቸው ተደጋጋሚ ጉዞዎች ዓለም አቀፍ ግኑኝነቶችን ለማጎልበት እና የኢንቨስትመንት ስምምነቶችን ለማሳከት ወሳኝ ናቸው ሲሉ ተከላክለዋል። በቻናል ቴሌቪዥን ፖለቲክስ ቱዴይ ላይ ቀርበው ባደረጉት ገለጻ፤ የጉዞዎቹን ጠቀሜታ ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ቲኒቡ በብራዚል ባደረጉት ጉብኝት 2 ቢልዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ማግኘታቸውን ተናግረዋል። አዲስ መሪ እንደመሆናቸው መጠን ግኑኝነቶችን ለማጠናከር እና እድሎችን ለመሳብ፤ ከዓለም መሪዎች ጋር መገናኘት አለባቸው ሲሉም ተከራክረዋል። የጉዞ ወጪን በተመለከተ የሚቀርቡ ስጋቶችን ውድቅ ያደረጉት ዩሱፍ ቱጋር፤ ከወጪው ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ እንደሚበልጥ አጽንኦት ሰጥተዋል። "ብዙ እየተጓዝን አይደለም። የተሻለ መስራት አለብን" ብለዋል ቱጋር። አ.አ.አ 2023 ወደ ሥልጣን የመጡት ቲኑቡ፤ 32 ጉዞዎችን አድርገው 19 ሀገራትን ጎብኝተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia