ኡጋንዳ 39ኛውን የድል ቀን አከበረች

ኡጋንዳ 39ኛውን የድል ቀን አከበረች ኡጋንዳ 39ኛ የድል ቀኗን እ.አ.አ በ1986 ከአምስት ዓመት የሽምቅ ውጊያ በኋላ ስልጣን የጨበጠውን ብሔራዊ የትግል ንቅናቄ እና የጦር ክንፉ የብሔራዊ ትግል ጦርን በማስታወስ አክብራለች። ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በሙበንዴ ብሔራዊ የመምህራን ኮሌጅ ግቢ የተካሄደውን የበዓል አከባበር መርተዋል። ሙሴቬኒ በንግግራቸው ለድሉ እና ለተከታታይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት አውቅና በመስጠት፤ ኡጋንዳ የተረጋጋች፣ ሰላማዊ እና ፈጣን እድገት ላይ የምትገኝ ሀገር እንደሆነች አጽንኦት ሰጥተዋል። ለሀብት ፈጠራ፣ ለብዝሃ ኢኮኖሚ፣ ለእሴት መጨመር እና እውቀት ላይ ለተመሠረተ ኢኮኖሚ ትኩረት ለመስጠት እንዳቀዱም ጠቁመዋል። በዝግጅቱ ላይ ባለፈው ዓመት የኡጋንዳን ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሳደጉ ናቸው የተባሉትን የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ እና የቡድን 77+ቻይና ጉባኤን በማዘጋጀት የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ 61 የመንግሥት ሰራተኞች ሜዳሊያ ተሸልመዋል። በበዓሉ ላይ የውጪ ዲፕሎማቶች፣ የገዥው ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል። የመጨረሻዎቹ ሁለት ፎቶዎች፦ ሙሴቬኒ በእርስ በርስ ጦርነቱ ወቅት እና በ1986 የፕሬዝዳንትነት ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik