ኢትዮጵያ እየተገበረቻቸው ባሉ ማሻሻያዎች ተግዳሮቶችን በማለፍ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ እየተገበረቻቸው ባሉ ማሻሻያዎች ተግዳሮቶችን በማለፍ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ነው ተባለ ኢትዮጵያ የኮቪድ ወረርሽኝ እና የአየር ንብረት ለውጥን የመሰሉ ተግዳሮቶችን በመቋቋም፤ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ኢኮኖሚ መሆን የቻለችው በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎቿ አማካኝነት ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ ተናግረዋል። ሀገራዊ ማሻሻያው የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባትን በመፍታት ገቢ እንዲጨምር አድርጓል ያሉት ሚኒስትሯ፤ ቀደም ሲል በዕዳ የተዘፈቀችው ኢትዮጵያ አሁን የንግድ ብድሮችን በማስቀረት በአምስት ዓመታት ውስጥ 10 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንደከፈለች እና ዕዳ-ከጂዲፒ ንፃሬ ከ30% ወደ 13.7% እንደቀነሰ ጠቁመዋል። ሀገሪቱ ከምትስበው በአማካይ 3 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ዓመታዊ የውጭ ኢንቨስትመንት እና በቁልፍ ዘርፎች ላይ ከተመዘገበው እድገት ጋር ተዳምሮ፤ ከሐምሌ 2024 ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው ማሻሻያ የውጭ ምንዛሪ ፍሰት ላይ ለውጥ እንዳመጣ ሚኒስትር ፍፁም ተናግረዋል። መንግሥት የውጭ ምንዛሪ ገበያውን ማረጋጋት እንደቻለ እና በማሻሻያው ወቅት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን አባወራዎች ለመደገፍ 3 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጎማ መመደቡንም አስታውቀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik