"ለሔር ኢሴ" የተሰጠው እውቅና ለቱሪዝም እድገት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተጠቆመ የ "ሔር ኢሴ" ባህላዊ ህግ በኢትዮጵያ፣ በጂቡቲ እና በሶማሊያ የጋራ ጥረት በተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ፣ የትምህርት እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ ቀደም ሲል ተመዝግቧል። የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ምዝገባው ባህሉን በሚገባ ለመጠበቅ፣ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ፣ የቱሪዝም እድገትን ለማፋጠን እና የጎረቤት ሀገራትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል። ሔር ኢሴ በኢትዮጵያ፣ ጂቡቲና ሶማሊያ ውስጥ የሚገኙትን የሶማሌ ኢሳ ማኅበረሰቦች የቃል ልማዳዊ ሕጎች ይመለከታል። በከፍተኛ ደረጃ የተደራጀና በጥብቅ የተሳሰረ ዲሞክራሲያዊ የአስተዳደር ሥርዓት ሲሆን፤ ሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ማለትም የፖለቲካ ሕገ ደንብ፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ እና የማህበራዊ ሥነ-ምግባር ደንብን ያካትታል።ምሥሎቹ ከዩኔስኮ ድረ-ገፅ የተገኙ ናቸው መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia