ንጉስ ቻርልስ ሶስተኛ ባለአግባብ የተያዙ ቅርሶችን እንዲመልሱ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጥያቄ ሊቀርበላቸው እንደሆነ ዘገባዎች አመለከቱተ የኢትዮጵያ መንግሥት ከ1868ቱ የመቅደላ ጦርነት በኋላ ተወስደው "ያለአግባብ" ብሪታንያ ውስጥ የቀሩ ቅርሶች እንዲመለሱ ለንጉስ ቻርልስ ሶስተኛ ጥያቄ እንደሚያቀርብ ሪፖርቶች ጠቆመዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት በእንግሊዝ የንጉሳዊ አገዛዝ ስብስብ ውስጥ የሚገኙ እንዲሁም በእንግሊዝ ውስጥ እንደ ብሪቲሽ ሙዚየም ባሉ ሌሎች ቦታዎች የሚገኙ ውድ ቅርሶች እንዲመለሱ ግፊት እንደሚያደርግ የእንግሊዝ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር በመሆን የማስመለስ ሂደቱን እንደሚመራ ዘ ቴሌግራፍ ዘግቧል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ዳይሬክተር ጄነራል አበባው አያሌው በቅርሶቹ ዙርያ በሰጡት አስተያየት "አግባብ አይደለም። የተቀደሱ ናቸው፤ ዝም ብለው በየትኛውም ቦታ የሚቀመጡ አይደሉም" ብለዋል። ኢትዮጵያ ቅርሶቹን ለማስመልስ በቅርቡ ለእንግሊዝ መንግሥት ይፋዊ ጥያቄ እንደምታቀርብ ነው የተገለጸው። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia