ኢትዮጵያ፣ ታንዛኒያ እና ኬንያ የሦስትዮሽ የኃይል ሽያጭ ሥምምነት ተፈራረሙ በስምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያ ለታንዛኒያ 100 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ታከናውናለች ተብሏል። ስምምነቱ በኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ላይ ያተኮሩ የህግ፣ የኮሜርሻል እና የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ መሠረት ያደረገ እንደሆነ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ተገልጿል። ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የታንዛኒያ የኤሌክትሪክ አቅራቢ ኩባንያ እና የኬንያ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኩባንያ ሲያካሂዱት የቆዩትን የሦስትዮሽ የኃይል ሽያጭ ድርድር ባጠናቀቁበት ወቅት ነው። የኃይል ሽያጭ ሥምምነቱ በሀገራቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፀድቆ ከሚያዝያ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል። የሦስትዮሽ ሥምምነቱ ኢትዮጵያ በኬንያ በኩል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የሚያስችላትን መብት የሚሰጣት እንደሆነ ተመላክቷል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia