የአሜሪካ ከአለም ጤና ድርጅት መውጣት የአፍሪካን የህብረተሰብ ጤና አደጋ ላይ ይጥላል ሲል የአፍሪካ ህብረት የጤና አካል አስታወቀ

የአሜሪካ ከአለም ጤና ድርጅት መውጣት የአፍሪካን የህብረተሰብ ጤና አደጋ ላይ ይጥላል ሲል የአፍሪካ ህብረት የጤና አካል አስታወቀ "የአፍሪካ አባል አገራት ለህብረተሰቡ ጤና የሚደረገውን የገንዘብ ድጋፍ ዳግም ለማጤን ጊዜው አሁን ነው" ሲሉ የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ነጋሺ ንጎንጎ ገልጸዋል። በሚቀጥለው ወር በአዲስ አበባ በሚደረገው የሀገራት መሪዎች ስብሰባ ወቅት በጉዳዩ ላይ እንደሚወያዩም ጠቅሰዋል።ሰኞ ዕለት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮቪድ-19 "ብልሹ አስተዳደር"፣ ማሻሻያ ማድረግ አለመቻል እና አላስፈላጊ የፖለቲካ ተፅዕኖን በመጥቀስ አሜሪካ ከአለም ጤና ድርጅ አባልነት መውጣቷን በይፋ ገልጸዋል። ትራምፕ ለአፍሪካውያን የኤች አይ ቪ/ኤድስ ህመምተኞች አስፈላጊ የሆነውን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የአስቸኳይ ጊዜ ዕቅድ ለኤድስ እርዳታ (PEPFAR) ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ ሊያቋርጡ ይችላሉ የሚል ስጋትም ተፈጥሯል።አሜሪካ ከጎርጎሮሳውያኑ 2024 እስከ 2025 22 በመቶ የሚሽፍን የአለም ጤና ድርጅት የግዴታ መዋጮዎች ኃላፊነት አለባት። ቻይና ደግሞ 16 በመቶ በማዋጣት ከአሜሪካ ቀጥላ እንደምትገኝ መገኛኛ ብዙሓን ዘግበዋል። በመሆኑም የአሜሪካ መውጣት ለዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ክፍተት ሊፈጥር ይችላል፣ በዚህም ከፍተኛ የበጀት ቅነሳ ሊያጋጥመው ይችላል። "ለዚያም ነው አፍሪካ ሲዲሲ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአፍሪካ ሀገራት በአካባቢው የህብረተሰብ ጤና ፋይናንስን ለማፋጠን የሚያስችሉ መንገዶችን እንዲያዘጋጁ ግፊት እየተደረገ ያለው ፤በዚህ ምክንያት በህብረተሰብ ጤና ጉዳይ የሚሰተጓጎል ነገር አይኖርም" ብለዋል ንጎንጎ።አሜሪካ በኮንግረስ የጋራ ውሳኔ በጎርጎርሳውያኑ 1948 ነበር የዓለም የጤና ድርጅት አባል የሆነውች እናም አሁን ከድርጅቱ ለመውጣት የአንድ ዓመት ጊዜ መስጠት ይጠበቅባታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik