ኢትዩጵያ የአለም የንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል የሁለትዩሽ ግንኙነቶችን ጀመረች

ኢትዩጵያ የአለም የንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል የሁለትዩሽ ግንኙነቶችን ጀመረችኢትዩጵያ የአለም የንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል ለምታደርገው ጥረት አምባሳደር ፅጋብ ክበበዉ የሁለትዩሽ ውይይቶችን ከጃፓን ፣ ሩሲያ እና የብሪታንያ አምባሳደሮች እና ቋሚ መልእከተኞች ጋር በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በውይይቶቹ ወቅት አምባሳደሩ ሀገራቱ ኢትዩጵያ የአለም የንግድ ድርጅትን እንድትቀላቀል እያደረጉ ላሉት አስተዋፃ አመስግነዋል። አምባሳደሩ ኢትዮጵያ ከየሀገራቱ ጋር ያላትን ታሪካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት አስረድተዋል።አክለውም ኢትዩጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ያለችበትን ሂደት አስረድተዋል። ኢትዩጵያ የአለም የንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል ወሳኝ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ እና ከወሳኝ የንግድ አጋሮች ጋር ሁለትዩሽ ውይይት በማድረግ ላይ መሆኗን አምባሳደር ፅጋብ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። አምባሳደሩ ውይይቶቹ በመጪው መጋቢት ሊካሄድ ከታቀደው አምስተኛው የፓርቲ ስራ ውይይት በፊት እንዲጠናቀቁ ጠይቋል። የጃፓን መልክተኛ የሆኑት ናኦኪ ሂኮታ ፣ የሩሲያ ፌድሬሽን መልክተኛ ኒኮላ ፕላቶኖቫ እና የብሪታንያው አንድሪው ጃክሰን በአጠቃላይ ኢትዩጵያ የአለም የንግድ ድርጅትን እንድትቀላቀል ያላቸውን ከፍተኛ ድጋፍ እና ግንኙነቱን ለማሳለጥ ያላቸውን ፍቃደኝነት አሳውቀዋል። አሁን ላይም የቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ያለቸውን ግብረመልስ እያዘጋጁ እና ድርድሮችን ለማነሳሳት ፍቃደኛ መሆናቸውን ለአምባሳደሩ አሳውቀዋቸዋል በማለት ፋና ዘግቧል። በተጨማሪም ባላቸው ግንኙነት የጉዳዩን አስቸኳይነት ግንዛቤን ለመፍጠር እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል። አምባሰደሮቹ ሀገራቶቻቸው ኢትዩጵያ የአለም የንግድ ድርጅትን እንድትቀላቀል ለማጋዝ ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik