ሩዋንዳ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ግጭታቸውን እንዲፈታ ፍላጎት ካለቸው ቱርክ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን የቱርክ ፕሬዝዳንት  አስታወቁ

ሩዋንዳ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ግጭታቸውን እንዲፈታ ፍላጎት ካለቸው ቱርክ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን የቱርክ ፕሬዝዳንት አስታወቁ " ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች በሚለው መርህ መሰረት ፤ በእኩል አጋርነት ላይ የተመሰረ ሁለቱንም የሚጠቅም እኛ የአህጉሪቱ መረጋጋት እና ልማት የሚያመጡ ጉዳዩች ላይ ድርሻችንን መወጣት እንፈልጋለን" በማለት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጠይብ ኤርዶዋን በአንካራ ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በአንድነት በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ተናግረዋል።በአንጎላ የሚመራውን የሩዋንዳ ኮንጎ ድርድር ቱርክ ድጋፍ እንደምትሰጠዉ ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል። ሁለቱ መሪዎች በንግድ እና ሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንዲሁም የቱርክ ድርጅቶች በሩዋንዳ ውስጥ ያላቸውን መገኘት እንዲጨምር እና የቱርክን ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ተነጋግረዋል።ካጋሜ በበኩላቸው ሩዋንዳ እና ቱርክ ትብብራቸውን ለማጠናከር ያላቸውን ትጋት በማስረጃ ያሰደገፉ ሲሆን ፤ ቱርክ ላላት ኢንቨስትመንት እና የአደራዳሪነት ሚና እንዲሁም ለኢትዮጵያን እና ሱማሊያ የስምምነት ፊርማ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን በአለም አቀፍ የደህንነት ጉዳዩች ላይ በራስ መተማመን እንዲሰፍን አሳስበዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik
ሩዋንዳ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ግጭታቸውን እንዲፈታ ፍላጎት ካለቸው ቱርክ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን የቱርክ ፕሬዝዳንት  አስታወቁ "ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች በሚለው መርህ መሰረት፤ በእኩል አጋርነት እና ሁሉኑም አሸናፊ በሚያደርግ ትብብር ለአህጉሪቱ መረጋጋት እና እድገት አስተዋጽኦ የማድረግ ግብ አስቀምጠናል ሲሉ" የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን በአንካራ ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር ሆነው በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ቱርክ አንጎላ ለምትመራው የሩዋንዳ-ኮንጎ ድርድር ድጋፍ እንደምትሰጠም ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል። ሁለቱ መሪዎች በንግድ እና ሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ስለማሳደግ የተወያዩ ሲሆን፤ የቱርክ ድርጅቶች ሩዋንዳ ውስጥ የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና በማንሳት የቱርክ ኢንቨስትመንት እንዲጨምር ተስማምተዋል። የተደረሱት ስምምነቶች ሩዋንዳ እና ቱርክ ትብብራቸውን ለማጠናከር ቁርጠኛ እንደሆኑ ያሳያል ያሉት ካጋሜ፤ ለቱርክ ኢንቨስትመንት እንዲሁም የሶማሊያ እና ኢትዮጵያን ስምምነት ጨምሮ፤ ለአንካራ የሰላም ጥረቶች ምስጋናቸውን ገልጸው፤ ዓለም አቀፍ የደህንነት ጉዳዩች በራስ ሊፈቱ ይገባል ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia