ግብፅ እና ሱማሊያ ግንኙነታቸውን በአዲስ እስትራቴጂካዊ የአጋርነት ስምምነት አደሱየግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲ የሱማሊያ አቻቸውን ሀሰን ሼህ ሞሀመድ በአል -ኢትሀድያ ቤተመንግስት በይፋዊ ስረአት ተቀብለዋቸዋል። የሁለትዩሽ ግንኙነቶችን እና በተስፋፋ ሁኔታ በልኡካኖቻቸው መሀከል የተደረገውን ውይይት ተከትሎ የእስትራቴጂካዊ ስምምነት እና በብዙ ጉዳዩች ላይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።ባለፈው ጥቅምት ወር ተካሄደው ውጤታማ የአስመራ የሶስትዩሽ (ግብፅ ፣ ሱማሊያ እና ኤርትራ) ጉባኤ በኋላ መሪዎቹ ለበለጠ ትብብር ሁለተኝ ጉባኤ ለማድረግ ወስነዋል። የካይሮ መቀዲሾ የአየር ጉዞ ከተጀመረ በኋላ ያላቸውን የሁለትዩሽ ግንኙነት ሂደት ገምግመዋል።በጤና ፣ በፍትህ ፣ በአቅም ግንባታ እና የጦር ጉዳዩች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሻሻል ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን፤ ይህም የጦር ትብብር ትግበራ የሱማሊያን ደህንነት ለማረጋግጥ እና በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት የሱማሊያ ተልእኮ ውስጥ ያላትን ተሳትፎ የሚያመቻች ነው። አል ሲሲ በቅርቡ የተፈረመውን ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ የሚሰጥ ስልጠናን እና ያለ ቪዛ የመጓዝ መብትን አሞግሰዋል። አክለውም የግብፅ እና ሱማሊያን ትብብር ለማጠናከር ግብፅ የሱማሊያ ደህንነት እና መረጋጋት እንዲፈጠር እርዳታዋን እንደምትቀጥል ፤ ይህም ለግብፅ ብሄራዊ ጥቅም አስፈላጊ መሆኑን በአፅንኦት ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia