ናይጄሪያ የካቲት 22 ጀምሮ ሁሉንም የቪዛ አገልግሎት ሂደቶች በበየነመረብ ስረአት ላይ ማድረግ ልትጀምር ነውይህንን አዲስ አሰራር የናይጄሪያ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ኦሉቡንሚ ቱንጂ - ኦጄ በኤክስ (የቀድሞ ቲዊተር) ላይ ከተፅእኖ ፈጣሪው ዶክተር ሴጉን አዎሳንያ ጋር በነበራቸው ውይይት ወቅት ነው ያሳወቁት። ማእከላዊ የቪዛ ሂደት ማከናወኛ ቢሮ ለመክፈት በእንቅስቃሴ ላይ መቆየታቸውን እና ይህም የቪዛ አሰጣጥን ወጥ በሆነ መንገድ ፣ የሀገርን ብሄራዊ ደህንነት ባረጋገጠ መንገድ እና ሙስናን ለመቀነስ የሚያግዝ ይሆናል በማለት ባለስልጣኑ ተናግረዋል። ማእከላዊ የቪዛ ስረአት ሂደት መፈጠሩ በአስተዳደሩ ትልቅ ሰኬት መሆኑን ቱንጂ ኦጆ አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል ፤ ይህም የደህንነት እና የሙስናን ስጋቶችን ወጥ የሆነ ሂደት መኖሩ ይቀንሳቸዋል እንደ ሪፖርቶች ዘገባ። ይህ ተነሳሽነት በአጠቃላይ የቪዛ ስረአቱን የማጣራት ስርአቶች አካቶ የሚይዝ ነው።ሚኒስትሩ አክለውም ሁሉን ያማከለ የመረጃ ማእከል አቡጃ ውስጥ በሚገኘው ቦላ አህመድ ቲኑቡ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ማእከል ህንፃ ላይ መመስረቱን አስታውቀዋል። ይህ 8.3 ፔታባይት ማእከል በናይጄሪያ የኢምግሬሽን አገልግሎት ውስጥ የነበረውን የመረጃ ክምችት ትክክለኛ ቦታ ለማስያዝ ይረዳል ፤ ይህም የግለሰብን መረጃ የመያዝ ደንብ በመተላለፍ በኮንትራክተሮች ጋር ሲቀመጥ የቆየውን የመረጃ ክምችት ያስቀራል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia