ኢትዩጵያን በቱርክ ስኪ ሪዞርት ሆቴል ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የተሰማትን ሀዘን ገለፀችየኢትዩጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቱርክ ቦሉ ግዛት በስኪ ሆቴል ሪዞርት እሳት አደጋ ህይወታቸው ላለፉ ሰዎች ወዳጅ ቤተሰቦች መፅናናትን በድንገተኛው የእሳት አደጋ ለቆሰሉት በፍጥነት እንዲያግሙ በመመኘት ሀዘኑን ገልጿል። በትላንትናው ምሽት በወጣው የሀዘን መግለጫ ላይ ሚኒስቴሩ በተከሰተው አደጋ ከቱርክ ህዝብ እና መንግስት ጎን በመቆም አጋርነቱን እንደሚያሳይ በመግለጫው አትቷል። በቦሉ ግዛት ከሚገኘው የሰኪ ሪዞርት በሚወጡ ሪፖርቶች መሰረት በትላንትናው እለት በተነሳው አደጋ በርካታ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ በእረፍት ላይ የነበሩ ብዙ ሰዎች ከእሳቱ ጭስ ለማምለጥ በመስኮቶች ሲዘሉ ታይተዋል። ማክሰኞ ጠዋት ላይ በካርትልካያ ሪዞርት በተነሳው እሳት 76 ሰዎች ሲሞቱ 51 ሰዎች አደጋ ደርሶባቸዋል በማለት የቱርክ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር አሊ ይርሊካያ ተናግረዋል። ብዙ ህፃናት የአደጋው ተጎጂ እንደሆኑ ይታመናል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia