የአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያና ላቲን አሜሪካ መሪዎች ለዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

የአፍሪካ፣ የአውሮፓ፣ የእስያና የላቲን አሜሪካ መሪዎች ለዶናልድ ትራምፕ እንኳን ደስ ያለህ መልዕክት አስተላለፉ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በደቡብ አፍሪካ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን የጠበቀ እና የጋራ ተጠቃሚነት ያለው አጋርነት ለመቀጠል እንደሚጠብቁ ተናግረዋል። የቡሩንዲው ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንዳይሺሚዬ ለትራምፕ "ደማቅ እንኳን ደስ አለዎት" በማለት በአለ ሲመታቸውን "ታሪካዊ" ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም "የስልጣን መንበሩን በመያዙ በቡሩንዲ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ትስስር ለማጠናከር እንጠብቃለን" ብለዋል። የግብፁ ፕሬዚዳንት አል ሲሲ ለትራምፕ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማጠናከር ከአዲሱ የአሜሪካ መሪ ቀጣይነት ያለውን ትብብር ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። የሁለቱን ህዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የጋራ ጥቅሞችን የማሳደግ እና በቀጠናው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ጸጥታ እና መረጋጋትን የማጎልበት ግብ ላይ አፅንዖት ሰጥተዋል። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ፣ የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉኡዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ፣ የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ፣ የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ፣ የሮማኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርሴል ቺዮላኩ፣ የፖላንድ ፕሬዝዳንት አንድሬጄ ዱዳ፣ የቼክ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ፣ የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ሉክሰን፣ የእንግሊዝ ንጉስ ቻርልስ ሶስተኛ፣ የፊንላንድ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ስቱብ፣ የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር ኡልፍ ክሪስተርሰን እና የአይስላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ክሪስትሩን ፍሮስታዶቲር እና ሌሎችም መሪዎች ለትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎች መልዕክት ካስተላለፉት መካከል ይገኛሉ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik
የአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያና ላቲን አሜሪካ መሪዎች ለዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የደቡብ አፍሪካ እና አሜሪካ የጠበቀ እና የጋራ ተጠቃሚነት ያለው አጋርነት ይቀጥላል ብለው እንደሚጠብቁ ገልጸዋል። የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኤቫሪስት ንዳይሺሚዬ ለትራምፕ "እንኳን ደስ አለዎት" በማለት በአለ ሲመታቸውን "ታሪካዊ" ብለውታል። አክለውም "በስልጣን ዘመንዎ የቡሩንዲ እና አሜሪካ የረጅም ጊዜ ትስስር እንደሚጠናከር እንጠብቃለን" ብለዋል። የግብፁ ፕሬዚዳንት አል ሲሲ ለትራምፕ ባስተላለፉት መልዕክት የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማጠናከር ከአዲሱ የአሜሪካ መሪ ጋር ትብብር ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። የሁለቱን ህዝቦች የጋራ ጥቅም የማሳደግ እና በቀጣናው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ጸጥታ እና መረጋጋትን የማጠናከር ግብ ላይ አፅንዖት ሰጥተዋል። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉኡዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ፣ የጀርመን መራሄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ፣ የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ፣ የሮማኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርሴል ቺዮላኩ፣ የፖላንድ ፕሬዝዳንት አንድሬጄ ዱዳ፣ የቼክ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ፣ የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ሉክሰን፣ የእንግሊዝ ንጉስ ቻርልስ ሶስተኛ፣ የፊንላንድ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ስቱብ፣ የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር ኡልፍ ክሪስተርሰን እና የአይስላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ክሪስትሩን ፍሮስታዶቲር እና ሌሎችም መሪዎች ለትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ካስተላለፉት መካከል ይጠቀሳሉ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia