የአፍሪካ ሴቶች በኪነጥበብ ሽልማት የጎርጎሮሳውያኑ 2024 ውድድር አሸናፊዎችን ይፋ አደረገ

የአፍሪካ ሴቶች በኪነጥበብ ሽልማት የጎርጎሮሳውያኑ 2024 ውድድር አሸናፊዎችን ይፋ አደረገ"እናት አፍሪካ" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው ከሳሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት ሴት አርቲስቶች የሚወዳደሩበት የ2024 የአፍሪካ ሴቶች በኪነጥበብ ሽልማት (AWAA) አርቲስቶች የአፍሪካን መገለጫዎች፣ ቅርስ እና የአህጉሪቱን ማንነት መንፈስ በፈጠራ ስራዎቻቸው እንዲመረምሩ እና እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል ሲሉ የውድድሩ አዘጋጆች ተናግረዋል። ከ11 ከሰሃራ በታች የአፍሪካ ሀገራት ከሚገኙ 36 አርቲስቶች መካከል ከናይጄሪያ፣ ዛምቢያ፣ ናሚቢያ እና ኢትዮጵያ የመጡ አሸናፊዎች አዲስ አርቲስቶች እና እስታብሊሽድ ማስተርስ ተብለው ተመድበዋል እናም የተለያዩ ባህላዊ ቅርሶችን እና ዘመናዊ አመለካከቶችን በኪነ-ጥበባቸው ይወክላሉ።ልዩ ሽልማትም የተሰጠ ሲሆን ሽልማቱ በአህጉሪቱ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰጥኦ ያላቸውን የአፍሪካ ሴት አርቲስቶች ሙያ ለማስተዋወቅ እና ለመደገፍ ያለመ ነው።"የፍፃሜ ተወዳዳሪዎቹ እና አሸናፊዎቹ መመረጥ ከአፍሪካ የመጡ ተሰጥኦ ያላቸው ሴት አርቲስቶችን በአህጉሪቱ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የምናደርገው ጥረት የመጀመሪያ እርምጃ ነው። ፋውንዴሽናችን እነዚህን ሴቶች ለመደገፍና ለማስተዋወቅ ዓመቱን ሙሉ ፕሮግራም ያካሂዳል። የአፍሪካ ሴቶች በኪነጥበብ ሽልማት እና የፋውንዴሽናችን ተነሳሽነት ሴቶች ጥበብን እንዲፈጥሩ እና የኪነ-ጥበባዊ ሥራዎቻቸውን እንዲቀጥሉ እድል እንደሚሰጣቸው እርግጠኛ ነኝ" ሲሉ የአፍሪካ ሴቶች በኪነጥበብ ሽልማት መስራች ያኒና ዱቤይኮቭስካያ ገልጸዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik