ሩሲያ እና ዚምባብዌ የጤና፣ የሕክምና ትምህርት እና የሳይንስ ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ በሁለቱ ሀገራት መንግሥታት መካከል የተደረገው ስምምነት፤ የሩሲያ ጤና ሚኒስትር ሚካሂል ሙራሽኮ እና የዚምባብዌው አቻቸው ዳግላስ ሞምቤሾራ ባደረጉት ውይይት ወቅት እንደተፈረመ፤ የሩሲያ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። "የዛሬው የትብብር ስምምነት ለቀጣይ እድገቶች መልካም ጅማሮ ነው" ሲሉ ሙራሽኮ በውይይቱ ላይ ተናግረዋል። እንደ መግለጫው ከሆነ ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት ቁልፍ የትብብር መስኮች ማለትም የዚምባብዌ ብሔራዊ የጤና ስርዓት አደረጃጀት፣ የጤና እንክብካቤ አስተዳደር፣ የበሽታ ሕክምና፣ የሕክምና መሳሪያዎች አቅርቦት እና ሳይንሳዊ ልውውጥ ላይ ያተኮረ ነው። ሁለቱ ወገኖች በሩሲያ ተቋማት የሕክምና ትምህርት እድል ዙርያ ትብብራቸውን ለመቀጠል ቃል ገብተዋል። "አሁን በሩሲያ ውስጥ 91 የዚምባብዌ ዜጎች የሕክምና ትምህርት እየተከታተሉ ይገኛሉ። ይህ የማደግ አቅም እንዳለው አይተናል" ሲሉ የሩሲያ የጤና ሚኒስትር ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia