በጋና ኦቡአሲ ማዕድን ማውጫ ላይ በተፈጠረ ግጭት የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ

በጋና ኦቡአሲ ማዕድን ማውጫ ላይ በተፈጠረ ግጭት የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ የጋና ጦር እንዳስታወቀው ባለፈው ቅዳሜ ወደ 60 የሚጠጉ ግለሰቦች የማዕድን ማውጫውን አጥር ጥሰው በወታደሮች ላይ ተኩስ ከከፈቱ በኋላ ሰባት ሕገ-ወጥ ማዕድን አውጪዎች ሲገደሉ፤ አንደኛው ላይ ጉዳት ደርሷል። ወታደሮቹ እራሳቸውን ለመከላከል እርምጃ መውሰዳቸውንና በተኩስ ልውውጡ አንድ ወታደር መቁሰሉን ጦሩ ባወጣው መግለጫ ገልጿል። ድርጊቱን “አሳዛኝ” ያለው የሀገሪቱ የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት፤ እውነቱን ለማጣራት አፋጣኝ ምርመራ ጀምሯል። የጋና አነስተኛ ማዕድን አውጪዎች ብሔራዊ ማህበር በበኩሉ ለምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ፤ ወታደሮቹ ዘጠኝ ያልታጠቁ ግለሰቦችን እንደገደሉ እና አስራ አራት ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቋል። የኦቡአሲ ማዕድን ማውጫበጆሃንስበርግ-የተመዘገበው የአንግሎጎልድ አሻንቲ ንብረት ሲሆን በጋና ቁልፍ የወርቅ ማውጫ ስፍራ ነው። መንግሥት ሕገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮዎችን ለመከላከል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የጸጥታ ኃይሎችን ማሰማራት እንደጀመረ ይነገራል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik