ግሪንላንድ ከዴንማርክ ጋር በደሴቲቱ ነፃነት ዙርያ መነጋገር መጀመር አለባት ሲሉ አንድ የህግ አውጪ ተናገሩ "እንደየኔ የግል አስተያየት ሉዓላዊ የግሪንላንድ ሀገርን በመመሥረት ዙርያ ከዴንማርክ ጋር በይፋ መነጋገር መጀመር አለብን። ህዝበ ውሳኔ ከማካሄዳችን በፊት መታወቅ ያለባቸው ብዙ አማራጮች አሉ። ለዚህም ነው የኔ ፓርቲ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብታችንን በተመለከተ በፓርላማ የውሳኔ ሀሳብ ያቀረበው" ሲሉ የግሪንለንድ ጥምር መንግሥት ሲዩሙት ሕግ አውጪ ኩኖ ፌንከር ለአርአይኤ ኖቮስቲ አስታውቀዋል። ዴንማርክ የደሴቲቱ የነጻነት ጥያቄ በተነሳ ቁጥር ግሪንላንድን ለዓመታት ስታስፈራራ እንደቆየች፤ የግሪንላንድ ፓርላማ አባል፣ የተቃዋሚው ናሌራክ ፓርቲ ሊቀመንበር እና የቀድሞው የግሪንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔሌ ብሮበርግ ለአርአይኤ ኖቮስቲ ቀደም ሲል ተናግረዋል። ℹ ግሪንላንድ እ.አ.አ እስከ 1953 ድረስ በዴንማርክ ቅኝ ግዛት ስር ነበረች። የዴንማርክ ንጉሣዊ አገዛዝ አካል ሆና ብትቆይም፤ በ2009 ራስን በራስ የማስተዳደር እና የውስጥ ፖሊሲዋን በተመለከተ የመወሰን መብት አግኝታለች። በ2019 ትራምፕ ግሪንላንድን ለመግዛት እያሰቡ እንደሆነ በተከታታይ በሚዲያዎች መዘገቡ የሚታወስ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia