በምሥራቅ ኡጋንዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 28 ደረሰ

በምሥራቅ ኡጋንዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 28 ደረሰ ሁለት የሶስት ዓመት ወንድ ልጆች አስከሬን በምሥራቃዊ ኡጋንዳ ጭቃ ውስጥ መገኘታቸውን ተከትሎ፤ ባለፈው ሳምንት በደረሰው የመሬት መደርመስ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 28 መድረሱን ፖሊስን ጠቅሰው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። እሮብ እለት በኤልጎን ተራራ ዳገት ላይ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት በርካታ መንደሮችን ቀብሯል። በቅድሚያ ከ100 የሚበልጡ ሰዎች እንደጠፉ እና 17 ሰዎች እንደሞቱ ተዘግቦ ነበር። እስካሁን ድረስ ተጨማሪ አስክሬኖች የተገኙ ሲሆን በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም የገቡበት አይታወቅም። በክልሉ ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የመሬት መንሸራተት ተከስቷል። የኡጋንዳ ቀይ መስቀል አስከፊው የአየር ሁኔታ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዘ ነው ብሏል። የኤልጎን ተራራ አካባቢ ከዚህ በፊትም እንዲሁ አደገኛ የመሬት መንሸራተት ታሪክ ያለው ሲሆን፤ በ2010 በተመሳሳይ አደጋ ቢያንስ 80 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik