የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት በቁጥጥር ስር በዋሉበት ፍርድ ቤት ደጋፊዎቻቸው ከባድ ግርግር ፈጠሩ ዩን ሱክ-ዮል አመጽ በመምራት ክስ መታሰራቸውን ተከትሎ፤ ደጋፊዎቻቸው በሲኦል ምዕራባዊ ዲስትሪክት ፍርድ ቤት በሀይል በመግባት ትርምስ ፈጥረው እንደነበር ዮንሃፕ የዜና አገልግሎት ዘግቧል። እንደ ኤጀንሲው ዘገባ ከሆነ፤ የተቆጣው ህዝብ ፖሊስን በመቋቋም መስኮቶችን ሰባብሮ ወደ ህንጻው ከገባ በኋላ፤ መስታወት እና የቢሮ እቃዎችን በእሳት ማጥፊያ እና ሌሎች መሳሪያዎች በመሰባበር "ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ-ዮል" በማለት ጩኸታቸውን ያሰሙ እንደነበር ተገልጿል። በአካባቢው በፍጥነት የደረሱ ሕግ አስከባሪዎች ሁከት ፈጣሪዎችን በማሰር፤ በህንፃው ውስጥ የቀሩት በአስቸኳይ እንዲለቁ፣ ከፍርድ ቤቱ እንዲበተኑ፣ ያልተፈቀደው ሰልፍ እና ሌሎች ሕገ-ወጥ ድርጊቶች እንዲቆም ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ የሙስና ምርመራ ቢሮ የሀገሪቱ ስልጣን በኃይል ለመያዝ ሞክረዋል ተብለው የተጠረጠሩት ፕሬዝዳንት እንዲያዙ ያቀረበውን ጥያቄ ቅዳሜ እለት ተቀብሏል። በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ ከተለቀቁ ጥፋተኝነታቸውን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ለማጥፋት ሊሞክሩ ይችላሉ ሲሉ መርማሪዎች ካቀረቡት አስተያየት ጋር ተስማምቷል። የዩን እስር የሙስና ምርመራ ቢሮው ፕሬዝዳንቱን ስልጣን በኃይል ለመያዝ በመሞከር ከከፈተባቸው ምርመራ የመነጨ ነው። ፕሬዝዳንቱ የፍርድ ሂደታቸው እስኪከፈት ድረስ ረዘም ያለ የእስር ጊዜ ይጠብቃቸዋል። የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቀረበባቸው የአመጽ ክስ ላይ እስከ ነሀሴ ወር ድረስ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ተንቀሳቃሽ ምስሉ ከማህበራዊ ትስስር ገጾች የተገኙ ናቸውበእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia