የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በቅርቡ በዩክሬን እና እንግሊዝ መካከል የተፈረመውን የ '100 ዓመት አጋርነት' ስምምነት ተቹ

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በቅርቡ በዩክሬን እና እንግሊዝ መካከል የተፈረመውን የ '100 ዓመት አጋርነት' ስምምነት ተቹ ቃል አቀባይዋ ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፦ ስምምነቱ ተቀባይነት የለውም ያሉት ዛካሮቫ ትርጉም የለሽ እና ውጤት አልባ ነው በማለት ውድቅ አድርገውታል። የብሪታንያ ተሳትፎ በአዞቭ-ጥቁር ባህር አካባቢ ያለውን ቦታ ለመያዝ ያላትን የረጅም ጊዜ ምኞት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል። ዩክሬን እና ብሪታንያ በአዞቭ ባህር ላይ ለመተባበር ምንም አይነት ህጋዊ መሰረት እንደሌላቸው ገልጸዋል። ዛካሮቫ ስምምነቱ የዩክሬን መንግሥት የህዝብ ግኑኝነት ስልት እና ጠንካራ ጥምረት እንደፈጠረ ለማስመሰል የሚደረግ ጥረት ነው ብለዋል። ስምምነቱ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ሐሙስ እለት ዩክሬንን በጎበኙበት ወቅት ነበር የተፈረመው። ይፋ የሆነው ሰነድ በዩክሬን የጦር ሰፈሮችን በማቋቋም እና በረጅም እርቀት የጦር መሳሪያዎች ዙርያ ትብብር ለማድረግ የተቀመጡ እቅዶችን ይዘረዝራል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik