የሞሪሸስ ጠቅላይ ሚኒስትር የቻጎስ ደሴት የኪራይ ስምምነት ላይ ጥያቄ አነሱ የሞሪሸሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቪን ራምጎላም የቻጎስ ደሴቶች ርክክብን በተመለከተ፤ የድርድሩ ቁልፍ ጉዳይ በሆነው የአሜሪካ እና ብሪታንያ የጦር ሰፈር የኪራይ ውል ጊዜ ላይ ተቃውሞ አንስተዋል። በጥቅምት ወር ብሪታንያ የቻጎስ ደሴቶችን ለሞሪሸስ ለማስረከብ ተስማምታ የነበረ ሲሆን፤ እስካሁን ባልፀደቀው ስምምነት መሰረት የዲዬጎ ጋርሺያን የጦር ሰፈር በ99 ዓመት የኪራይ ውል ለመቆጣጠር ያስችላታል። የህዳሩን ምርጫ አሸንፈው ስልጣን የያዙት ጠቅላይ ሚኒስትር ራምጎላም ስምምነቱን ተችተዋል። የብሪታንያን ስምምነት “የክህደት” ነው ሲሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ራምጎላም፤ የኪራይ ውሉ የዋጋ ንረት እና የምንዛሪ ተመንን ሊያካተት፣ እንግሊዝ ውሉን በራሷ እንዳታድስ ሊገድብና ለሞሪሸስ ሉዓላዊነት እውቅና ሊሰጥ ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል። ሉዓላዊነት አስፈላጊ እንደሆነ አፅንዖት የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ስምምነቱ ከትራምፕ ሥልጣን በፊት እንዲጠናቀቅ ትፈልጋለች ብለዋል። የትራምፕ እጩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፤ የቻጎስ ደሴቶች ስምምነት የጦር ሰፈሩን ከቻይና ጋር ወዳጅ ለሆነ ሀገር አሳልፎ የሚሰጥና የአሜሪካን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia