የሩሲያ እና ኢራን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ስምምነት ቁልፍ ነጥቦች፦ 🟠 ከሁለቱ ወገኖች አንዱ ከተጠቃ ሌላኛው ለጠብ አጫሪው ምንም አይነት ድጋፍ ሊያደርግ አይገባም። 🟠 ሩሲያ እና ኢራን የዓለም ደህንነትን ለማስጠበቅ አስፈላጊ አካል እንደሆነ ግምት ውስጥ በማስገባት ወታደራዊ-ቴክኒካዊ ትብብራቸውን ለማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። 🟠 ሀገራቱ የጋራ ወታደራዊ ልምምድን በተመለከተ በቅርበት ለመስራት ተስማምተዋል። 🟠 ሞስኮ እና ቴህራን የሶስተኛ ሀገር ማዕቀቦችን በስራ ላይ ከማዋል ለመቆጠብ እና የአንድ ወገን አስገዳጅ እርምጃዎችን ተግባራዊ ላለማድረግ ዋስትና ይሰጣሉ። 🟠 ሩሲያ እና ኢራን ከሶስተኛ ሀገራት ነፃ የሆነ የክፍያ መሠረተ ልማት በመፍጠር ዙርያ ለመተባበር ተስማምተዋል። 🟠 ሞስኮ እና ቴህራን በጦር መሳሪያ ቁጥጥር፣ በትጥቅ ማስፈታት እና ዓለም አቀፍ ደህንነትን ለማረጋገጥ እንደሚተባበሩ ገልጸዋል። 🟠 ሞስኮ እና ቴህራን ሀሰት መረጃዎችን እና አሉታዊ ፕሮፖጋንዳዎችን ለመከላከል በሁለቱ ሀገራት ሚዲያዎች መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግ ተስማምተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia