ፕሬዝዳንት ቱዋዴራ የሩሲያ ባለሀብቶች በማዕከላዊ አፍሪካ መዋዕለ ነዋይ እንዲያፈሱ ጥሪ አቀረቡ

ፕሬዝዳንት ቱዋዴራ የሩሲያ ባለሀብቶች በማዕከላዊ አፍሪካ መዋዕለ ነዋይ እንዲያፈሱ ጥሪ አቀረቡ የሩሲያ ባለሃብቶች በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ "ግንኙነቶችን መገንባት፣ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክን በርካታ እምቅ አቅም ማስተዋወቅ" ይችላሉ ሲሉ፤ ፎውስታ አርካንጅ ቱዋዴራ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር ካደረጉት ውይይት በኋላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። "በፕሬዝዳንት ፑቲን ግብዣ መሰረት ወደ ሩሲያ ፌደሬሽን ያደረግነው ጉብኝት፤ ከፕሬዘዳንቱ ጋር ያደርግነው ግኑኝነት በሁሉም ደረጃ በተለይም በጸጥታ ትብብራችንን ለመጠናከር እድል ይሰጣል" ያሉት ቱዋዴራ፤ ሀገሪቱን ለአለመረጋጋት የዳረጋትን የ2020-2021 ጥቃት ጠቅሰዋል። ቱዋዴራ ግብርና፣ ማዕድንና መሠረተ ልማት ከሩሲያና ከባለሀብቶቿ ጋር ለመተባበር የሚያስችሉ መስኮች ናቸው ሲሉም በምሳሌነት አንስተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik