የኢትዮጵያ የማአድን ኢንዱስተሪ ከ1 ቢሊዩን ዶላር በማስገባተ ከፍተኛ እድገት ማሳየቱ ተዘገበ የኢትዮጵያ ማእድን ዘርፍ ባለፉት ስድስት ወራት ከአንድ ቢሊዩን ዶላር ማስገባቱን የማእድን ሚኒስቴር አስታወቀ። ምክትል ሚኒስትሩ ሚሊዩን ማቴዎስ እንዳሉት ይህ ገቢ በእቅድ ከተያዘዉ 376 ሚሊዩን ዶላር በ278 በመቶ ብልጫ ያለው ነው። ይህ ገቢ ለብሄራዊ ባንክ የተላለፈውን 16.9 ቶን ወርቅ ይጨምራል።ታንታለምን፣ ኦፓልን፣ ኦርናሜንታልስ፣ ላይምስቶን፣ ሊትየም ኦር እና የኢንዱስትሪ ማእድናትን ወደ ውጭ ለመላክ ከታሰበዉ እቅድ የሚበልጥ ገቢ ማግኘት ተችሏል። በዚህም ከ105 ቶን በላይ የታንታለም ምርት እና 2,071 ቶን ሊትየም ወደ ውጭ ተልኳል። ከኦርናሜንታልም እና ከብረት ምርት የወጪ ንግድ ከታቀደው 73 በመቶ 22.4 ሚሊዩን የተገኘ ሲሆን ይህም ከእቅድ በታች ነው። ሁለንታዊ የማክሮኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ በህገወጥ አውጭዎች ላየ የተደረገ እርምጃ እና አዳዲስ የማእድን መሸጫ መከፈታቸው ለለውጡ በምክንያትነት ተጠቅሷል። ዘርፉ 102,000 የስራ እድሎችን ባለፈዉ ስድስት ወር ፍጥሯል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia