የዩኬ መንግስት ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚያርፉበትን የሆቴል ቁጥር በመጪው መጋቢት ለመቀነስ ማቀዱ ተነገረ

የዩኬ መንግስት ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚያርፉበትን የሆቴል ቁጥር በመጪው መጋቢት ለመቀነስ ማቀዱ ባለስልጣኗ ተናገሩ " በመጪዉ መጋቢት መጨረሻ ዘጠኝ ሆቴሎችን ለመዝጋት እቅድ ተይዟል፤ በስድስት ጨምሮ የነበረው የነበረው ቁጥር በመጪው መጋቢት ጥቂት ሆቴሎች ብቻ ይቀሩታል" በማለት የዩኬ ምክትልየሀገር ውስጥ ጉዳዩች ሀላፊ አንጌላ ኤግል ለፓርላማው ተናግረዋል።መንግስት የጥገኝነት ጥያቄን ስረአት በማስተካከል እና የድንበር ላይ የፀጥታ ማዘዣዎችን በመፍጠር ህገወጥ የሰው አስተላላፊዎችን ለመዋጋት እና የጥገኝነት ጠያቂዎችን ቁጥር የመቀነስ ሀሳብ አለው በማለት ጨምራለች።ባለፈው የመኸር ወራት 220 ሆቴሎች ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞችን ይዘዉ ነበር በማለት ኤግል ተናግረዋል። ባለፈው ህዳር እንደተናገረችው ከሀምሌው ጠቅላላ ምርጫ በኋላ 14 ተጨማሪ ሆቴሎች ለዚሁ አገልግሎት እንደዋሉ ነገርግን ሰባቱ መዘጋታቸውን ጨምረው ተናግረዋል። ባለፈው ጥቅምት የዩኬ ብሄራዊ ኦዲት ቢሮ እንዳለው የሀገር ውስጥ ጉዳይ ቢሮ 4.7 ቢሊዩን (5.75 ቢሊዮን ዶላር) ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለመርዳት የወጣ ሲሆን በጎርጎሮሳዊያኑ 2023-2024 የፋይናንስ አመት ይህ ቁጥር 3 ቢሊዩን ፓውንድ (3.67 ቢሊዮን ዶላር) ለሆቴል ወጭ የተከፈለውን ይጨምራል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik
የዩኬ መንግስት ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚያርፉበትን የሆቴል ቁጥር በመጪው መጋቢት ለመቀነስ ማቀዱ ተነገረ"በመጪዉ መጋቢት መጨረሻ ዘጠኝ ሆቴሎችን ለመዝጋት እቅድ ተይዟል። በስድስት ጨምሮ የነበረው የነበረው ቁጥር በመጪው መጋቢት ይቀንሳል" ሲሉ የዩኬ ምክትል የሀገር ውስጥ ጉዳዩች ሚኒስትር አንጌላ ኤግል ለፓርላማ ተናግረዋል።መንግስት የጥገኝነት ጥያቄ ስርዓትን በማሻሻል እና የድንበር ላይ የፀጥታ ዕዞችን በመፍጠር ሕገ-ወጥ የሰው አስተላላፊዎችን ለመዋጋት እና የጥገኝነት ጠያቂዎችን ቁጥር የመቀነስ እቅድ እንዳለው ጨምረው ገልጸዋል።ባለፈው የጸደይ ወር 220 ሆቴሎች ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞችን ለማስተናገድ እንደዋሉ ኤግል ተናግረዋል። ከሀምሌው ጠቅላላ ምርጫ በኋላ 14 ተጨማሪ ሆቴሎች ለዚሁ አገልግሎት እንደዋሉና ሰባቱ ደግሞ መዘጋታቸውን አክለዋል። የሀገር ውስጥ ጉዳይ ቢሮ ለጥገኝነት ጠያቂዎች ድጋፍ በጎርጎሮሳዊያኑ 2023-2024 የበጀት አመት 4.7 ቢሊዮን ፓውንድ (5.75 ቢሊዮን ዶላር) እንዳወጣና ከዚህ ውስጥ 3 ቢሊዮን ፓውንድ (3.67 ቢሊዮን ዶላር) የሆቴል ወጪ እንደሆነ፤ የዩኬ ብሄራዊ ኦዲት ቢሮ ባለፈው ጥቅምት ወር አስታውቆ ነበር።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ   @sputnik_ethiopia