ሩሲያ ከመካከለኛው ምስራቅ አትወጣም፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቭሮቭ በሶሪያ እና ስለ ወደፊቱ የሩሲያ እና የአረብ ሀገራት ውይይት ዙሪያ የተናገሩት “ከመካከለኛው ምስራቅ አንወጣም። እውነት ነው ሶሪያ ውስጥ የተከሰቱ ነገሮች አሉ። ፕሬዚዳንቱ እንዲሁም አንዳንድ ተወካዮቻችን በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተውበታል። ይህ የተፈጠረው ባለፉት አመታት፤ ባለፉት አስርት አመታት በሶሪያ አረብ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጥያቄ መሰረት ወታደሮቻችንን ወደዚያ ከላክንበት ጊዜ ጀምሮ እና ከቱርክ እና ኢራን እንዲሁም ከበርካታ የአረብ ሀገራት ጋር በመሆን አማራጭ ማዕቀፍ ከፈጠርን በኋላ ባሉት ጊዜያት የፖለቲካ ሂደት መቀዛቀዝ ነበር። ምናልባትም ምንም ነገር ላለመቀየር ፍላጎት ነበር። ይህ ስህተት ነው ብለን አናስባለን። ለመከላከልም ሞክረናል" ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia