የአለም ጤና ድርጅት ከታህሳስ ወር መጀመሪያ ጀምሮ በአፍሪካ ከ1,500 በላይ ሰዎች በኤምፖክስ በሽታ መያዛቸውን ገለጸ

የአለም ጤና ድርጅት ከታህሳስ ወር መጀመሪያ ጀምሮ በአፍሪካ ከ1,500 በላይ ሰዎች በኤምፖክስ በሽታ መያዛቸውን ገለጸየዓለም የጤና ድርጅት በተለይ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሽታው የመከሰት መጠኑ ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል። ድርጅቱ ባወጣው መረጃ መሰረት ከጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ጥር 1፣ 2024 እስከ ጥር 5፣ 2025 ድረስ በአፍሪካ 14,700 ሰዎች በኤምፖክስ (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) በሽታ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 66 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል።ይህም ከታህሳስ 1 ቀን ጋር ሲነፃፀር 1,529 ተጨማሪ ሰዎች ሲያዙ 9 ተጨማሪ ሞት ያስከተለ ነው። በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ካለፈው የጎርጎሮሳውያን ኅዳር 25 ጀምሮ 2,464 ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን፣ በቡሩንዲ 798፣ በኡጋንዳ 767፣ በሩዋንዳ 17 እና በኬንያ 12 ሰዎች ተይዘዋል።በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከጥር 1፣ 2022 እስከ ህዳር 30፣ 2024 ድረስ በዓለም ዙሪያ በ127 አገሮች ውስጥ 117,663 ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 263 ሰዎች ሞተዋል። ለዚህ በሽታ በመጀመሪያ እንደ አለም አቀፍ የጤና ስጋት ከሐምሌ 2022 እስከ ግንቦት 11 ቀን 2023 ድረስ ተፈፃሚ ተደርጎ ነበር። በቫይረሱ ስርጭት መቀነስ ምክንያት የተቋረጠ ቢሆንም ነሐሴ 14 ቀን 2024 የዓለም የጤና ድርጅት ኃላፊ በአፍሪካ በተከሰተው ወረርሽኝ ምክንያት እንደገና አስጀምረውታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik