ቬንዙዌላ ከብሪክስ ጋር በመሆን የባለብዙ ዋልታ ዓለም ግንባታ ላይ ለመሳተፍ እንዳቀደች ፕሬዝዳንት ማዱሮ ተናገሩ

ቬንዙዌላ ከብሪክስ ጋር በመሆን የባለብዙ ዋልታ ዓለም ግንባታ ላይ ለመሳተፍ እንዳቀደች ፕሬዝዳንት ማዱሮ ተናገሩ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር "ቀጣይ [የሚመጣው] ለውጥ ጂኦፖለቲካዊ ነው። ለአዲሱ ባለብዙ ዋልታ ዓለም ጅማሮ ሀይል መስጠት እና ቬንዙዌላም በአዲሱ የሰላም፣ የትብብር እና የእድገት ፖሊሲ ግንባር ውስጥ እንድትካተት ያስፈልጋል። ከብሪክስ ጋር አንድ ላይ በመሆን። አዲስ ታሪክ ከሚያራምደው ብሪክስ ጋር ከወዲሁ አብረን ነን" ብለዋል። ማዱሮ ከ2025 እስከ 2031 ለሚዘልቀው የስልጣን ዘመን አርብ እለት የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት በመሆን ተሹመዋል። "ለጥቂት ሰዎች፣ ለአንድ ቤተሰብ፣ ለበላይ ገዢዎች ወይም ለኢምፔሪያሊስቶች ፕሬዝዳንት ሆኜ አላውቅም፤ አልሆንምም። አንድ ባለቤት፣ አንድ አለቃ እና አንድ አዛዥ ብቻ ነው ያለኝ። ልቤ ታማኝነቱ ለአንድ ኃይል ነው፤ ይህም ኃይል ታሪካዊው ተራው ህዝብ ነው” ሲሉ ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ ተናግረዋል። በተጨማሪም የሩሲያ ፓርላማ ዱማ አፈ-ጉባዔ ቪያቼስላቭ ቮሎዲን እና ማዱሮ ከሹመት ሥነ-ሥነሥርዓቱ በኋላ በካራካስ ተገናኝተዋል። አፈ-ጉባዔው ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለማዱሮ የተላከ የእንኳን አደረስዎ መልዕክት አስተላልፈዋል። ቮሎዲን በቬንዙዌላ ቆይታቸው በማዱሮ ሹመት ላይ ከተገኙ የበርካታ ሀገራት የሕግ አውጭ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik