የናይጄሪያ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በሀገር ውስጥ ጥቅል ምርት ላይ በሚያደርገው ስሌት ሕገ-ወጥ እና ድብቅ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያካትት ገለጸ በብሔራዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ የብሔራዊ መዝገብ ክፍል ኃላፊው ባባ ማዱ "ሕጋዊ ድጋፍ የሌላቸው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች አሉ። ፈጻሚዎቹ ከነዚህ እንቅስቃሴዎች ገቢ በማግኘት በመደበኛ ሴክተር ውስጥ ከተሰማሩት በተሻለ ይኖራሉ። የኋላ ኋላ የተገኘው ገቢ በመደበኛው ኢኮኖሚ ላይ ተጽእኖ ያሳድራል" ብለዋል። በቅርቡ ይፋ የሚደረገው የናይጄሪያ ኢኮኖሚ ስሌት፤ ከተገመተው በላይ ትልቅ ኢኮኖሚ ሊያሳይ እንደሚችል እና በአሁኑ ወቅት ከአፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚዎች አራተኛ ላይ የተቀመጠችውን ናይጄሪያ፤ ደረጃዋን ከፍ ሊያደርግ እንደሚችል ማዱ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia