ቭላድሚር ፑቲን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመገናኘት ዝግጁ እንደሆኑ ክሬምሊን በድጋሚ ገለጸ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ፤ ሞስኮ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ውይይት ለማድረግ ፍላጎት በማሳየታቸው ደስተኛ ነች ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። "ቭላድሚር ፑቲን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ከዓለም መሪዎች ጋር ለመገናኘት ዝግጁ መሆናቸውን ደጋግመው ተናግረዋል" ብለዋል። ዶናልድ ትራምፕ ቭላድሚር ፑቲን ሊያገኟቸው እንደሚፈልጉ እና ሁለቱ መሪዎች ለመገናኘት ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ በዛሬው እለት ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia