ናይጄሪያ የተባበሩት መንግስሥታት ድርጅት በቦኮ ሃራም የሽብር ቡድን የገንዘብ ድጋፍ እና ስልጠና ዙርያ ምርመራ እንዲከፍት ጠየቀች የተባበሩት መንግሥታት የቦኮ ሃራምን የገንዘብ ድጋፍ ተከታትሎ ለማግኘት ጣልቃ መግባት አለበት ያሉት የናይጄሪያ የመከላከያ ሰራዊት አዛዥ ጄኔራል ክሪስቶፈር ሙሳ፤ ከአቅማቸው በላይ የሆነ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ፍሰት እንዳለ አስረድተዋል። “ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ተነጋግረናል። የገንዘቡን ምንጭ እንወቅ። እስካሁን ከ120,000 በላይ የቦኮ ሃራም አባላት እጃቸውን የሰጡ ሲሆን አብዛኞቹ ከጥሬ ገንዘብ ጋር ነው የተያዙት። እንዴት አገኙት? የገንዘብ ድጋፉን እንዴት ነው የሚያገኙት? ስልጠናውን እንዴት አገኙ? መሳሪያዎቹን ከየት አገኙት?" ሲሉ ጠይቀዋል። ሙሳ “እንዴት ለ15 ዓመታት መቆየት ቻሉ? ሁሉም ሰው ራሱን መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ነው” በማለት፤ ከጀርባ ዓለም አቀፍ ሴራ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል። ሙሳ ሀገሪቱ ከአሸባሪዎች ጋር ለምታደርገው ጦርነት የጋራ ልምምዶችን መቀጠል እና አስፈላጊ መሳሪያዎችን ማግኘቷ ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል። ናይጄሪያ የምትችለውን ብታደርግም፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ መሳሪያዎችን መግዛት ብዙ ጊዜ አዳጋች እንደሚሆንባቸውም ጄኔራሉ አብራርተዋል። ናይጄሪያ ራሷን ለመጠበቅ እና አፍሪካን ለመርዳት ያላትን አቅም በማጉላት፤ ሀገሪቱ የውጭ ሀገር የጦር ሰፈሮችን እንደማታበረታታ አስረግጠዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia