ሩሲያ ለስደተኞች የሚውል 1600 ቶን እህል ለኢትዮጵያ አስረከበች

ሩሲያ ለስደተኞች የሚውል 1600 ቶን እህል ለኢትዮጵያ አስረከበች የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በጋምቤላ ክልል ለሚገኙ ስደተኞች የተደረገውን እርዳታ በደስታ ተቀብሏል ሲል፤ በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ለሩሲያ መገናኛ ብዙሃን አስታውቋል። "ይህ ድጋፍ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የሚያቀርበው የምግብ እርዳታ መመናመን ባጋጠመው ወቅት መደረጉ በጣም ወሳኝ ነው። ከሩሲያ ፌዴሬሽን የተገኘው ድጋፍ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በጋምቤላ ክልል ለሚገኙ 163,240 ስደተኞች የምግብ ዕርዳታ ለማቅረብ ያስችለዋል" ሲል ኢምባሲው ተናግሯል። በዓለም ምግብ ፕሮግራም ድጋፍ የሚደረግላቸው አብዛኞቹ ስደተኞች፤ በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ምክንያት ከሚያስፈልጋቸው ዕለታዊ የተመጣጠነ ምግብ 60% የሚሆነውን ብቻ ያገኛሉ ብሏል ኤምባሲው። እ.አ.አ 1980ዎቹ በአስከፊው የኢትዮጵያ ረሃብ ወቅት የሶቭየት ህብረት ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጓን፤ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን አዳማ በተካሄደው የእህል ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ አስታውሰዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik