ማስጠንቀቂያ፦ አሰቃቂ ምስሎች

ማስጠንቀቂያ፦ አሰቃቂ ምስሎች በቻድ ፕሬዝዳንታዊ ቤተ-መንግሥት አቅራቢያ በደረሰ ጥቃት 18 አጥቂዎችን ጨምሮ 19 ሰዎች መሞታቸውን የቻድ መንግሥት አስታወቀ 🟠 ትናንት ምሽት ላይ በቻድ ኒጃሜና በሚገኘው ፕሬዝዳንታዊ ቤተ-መንግሥት አቅራቢያ በተካሄደ ጥቃት 18 አጥቂዎችን ጨምሮ 19 ሰዎች ተገድለዋል። የመንግሥት ቃል አቀባይ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው ጥቃቱ ገጀራና ቢላዋ በታጠቁ 24 ግለሰቦች እንደተፈጸመ ገልጸዋል። 🟠 ጥቃቱ የቻድ ፕሬዝዳንት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ በቤተ-መንግሥት ውስጥ በነበሩበት ወቅት እና የቻድ መሪዎች እና የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ እንደተፈጸመ ታውቋል። 🟠 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና የመንግሥት ቃል አቀባይ አብደራማን ኩልማላህ አጥቂዎቹ “ሙሉ በሙሉ በአደንዛዥ ዕፅ የደነዘዙ" የውንብድና ቡድን አባላቶች ናቸው ብለዋል። አክለውም በዲና መኪና እንደመጡና አራት ጠባቂዎችን በስለት ወግተው አንዱን እንደገደሉና ሁለቱን በክፉኛ አቁስለው ቀሪው ላይ ለሕይወት አስጊ ያልሆነ የአካል ጉዳት ማድረሳቸውን ገልጸዋል። 🟠 ከቦኮ ሃራም ጋር ግንኙነት ሊኖር ይችላል የሚል ወሬ እየተናፈሰ ቢሆንም ኩልማላህ ጥቃቱ “ምናልባትም የሽብር ላይሆን ይችላል” ብለዋል። በፕሬዝዳንቱ እንደተገለጸው “ፍፁም የተስፋ መቁረጥ ጥቃት” ነው ብለውታል። 🟠 የፖሊስ ጣልቃ ገብነትን ተከትሎም ሁኔታው ​​በቁጥጥር ስር ውሏል። ከተገደሉት 18 አጥቂዎች በተጨማሪ 6ቱ ቆስለዋል። ፕሬዝዳንቱን ያጣቀሱት ኩልማላህ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እና በተቋማት ላይ ምንም አይነት ስጋት እንደሌለ ተናግረዋል። 🟠 በድርጊቱ ዙርያ ምርመራ እንደተጀመረ ኩልማላህ ጨምረው ገልጸዋል። በኒጃሜና ፕሬዝዳንታዊ ቤተ-መንግሥት አቅራቢያ የደረሰውን ጥቃትና የተገደሉ አጥቂዎችን አስከሬን የሚያሳይ ቪዲዮ ስፑትኒክ ደርሶታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik