ኢትዮጵያ ያሏትን የቱሪስት መዳረሻዎች ደረጃ በማሳደግ እና አዳዲስ የቱሪስት መስህቦችን በማልማት የአፍሪካ ዋና የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን ማቀዷ ተገለጸ

ያሏትን የቱሪስት መዳረሻዎች ደረጃ በማሳደግ እና አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋና የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን እቅድ አላትየቱሪዝም ልማት የአካባቢው ነዋሪዎች መጠቅም አለበት በማለት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ተናገሩ። ሚኒስትሯ ይህንን የተናገሩት ከወጥ አለት ተፈልፍሎ በተሰራው በጥንታዊዉ እና የገና በአል በድምቀት በሚከበረበት የላሊበላ ቅዱስ አብያተ ክርስትያን በነበራቸው ቆይታ ነው። ሚኒስትሯ እንደ ዩኔስኮ ካሉ ድርጅቶች ጋር የሚደረጉ አጋርነቶች በአማራ ክልል የባህላዊ ቅርሶች ስፍራዎችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል ወሳኝ እንደሆኑ ተናግረዋል። አክለውም እነዚህ የሚደረጉ ማሻሻያዎች ባህላዊ ክብረበአላትን በማስተዋወቅ ተጨማሪ ጎብኚዎችን ለመሳብ ይረዳሉ ብለዋል።ከዚህ በበለጠ ፤ የቱሪዝም ኢንቨስትመንትን ማሳደግ አገልግሎት አቅራቢዎች ኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የሚያጠናክር የውጭ ምንዛሬ እንዲያመነጩ ያደርጋቸዋል በማለት ሰላማዊት ካሳ ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ በአካታች ልማት እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በአለም ላይ ያላትን ገፅታ በማሻሻል ፤ የአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ሆና ለመገኘት ያላትን ፍላጎት ሚኒስትሯ በአፅንኦት አስረድተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik
ኢትዮጵያ ያሏትን የቱሪስት መዳረሻዎች ደረጃ በማሳደግ እና አዳዲስ የቱሪስት መስህቦችን በማልማት የአፍሪካ ዋና የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን ማቀዷ ተገለጸየቱሪዝም ልማት የአካባቢውን ማህበረሰብ መጥቅም አለበት ሲሉ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ተናግረዋል። ሚኒስትሯ ይህንን የተናገሩት ከወጥ አለት ተፈልፍሎ በተሰራው በጥንታዊዉ እና የገና በዓል በድምቀት በሚከበረበት የላሊበላ ቅዱስ አብያተ ክርስትያን በነበራቸው ቆይታ ነው። ሚኒስትሯ እንደ ዩኔስኮ ካሉ ድርጅቶች ጋር የሚደረጉ አጋርነቶች በአማራ ክልል የባህላዊ ቅርሶች ስፍራዎችን መሰረተ ልማት ለማደስ ወሳኝ እንደሆኑ ተናግረዋል። አክለውም እነዚህ እድሳቶች ባህላዊ ክብረ በአዓትን በማስተዋወቅ ተጨማሪ ጎብኚዎችን ለመሳብ ይረዳሉ ብለዋል።የቱሪዝም ኢንቨስትመንትን እና አገልግሎት አቅራቢዎች ማጠናከር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የውጭ ምንዛሬ እንዲያመነጭ ያደርጋል በማለት ሰላማዊት ካሳ አብራርተዋል። ኢትዮጵያ በአካታች ልማት እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በአለም ላይ ያላትን ገፅታ በማሻሻል፤ ቀዳሚ የአፍሪካ የቱሪስት መዳረሻ የመሆን ፍላጎት እንዳላት ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia