ከቻድ ተከትላ የፈረንሳይ ጦር እንዲወጣ መወሰኗ "በድርድር" ነው በማለት ኢማኑኤል ማክሮን መናገራቸውን ሴኔጋል ነቀፈችው " ይህ መግለጫ ሙሉ በሙሉ ስህተት ነው። እከዛሬ ድረስ የተደረገ ውይይት ሆነ ድርድር የለም ፤ ውሳኔው በብቸኝነት እንደ ነፃ ፣ ገለልተኛ እና ሉአላዊ ሀገር ሴኔጋል ወስናለች" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ኦስማኔ ሶንኮ በትላንትናው እለት አረጋግጠዋል።የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት አማኑኤል ማክሮን ማንኛውም የአፍሪካ ሀገር ያለ ፈረንሳይ ጣልቃገብነት ሉአላዊ አይደለም ፤ በማለት የተናገሩትን ንግግር የተቃወሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ሶንኮ ፈረንሳይ "የአፍሪካን ደኅንነትና ሉዓላዊነት የማረጋገጥ አቅምም ሆነ ሕጋዊነት የላትም" በማለት ተናግረዋል። ሶንኮ ፈረንሳይ " ለተወሰኑ ሀገራት ሰላም ማጣት በተደጋጋሚ ጊዜ የራሷን ድርሻ ተወጥታለች" በተለይም በሳህል ቀጠና ያለው የፀጥታ ሁኔታ በሚታይ መልኩ እንዲባባስ አድርጋለች በማለት ይከራከራሉ።በአጠቃላይ የሴኔጋሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ የኢማኑኤል ማክሮንን ንግግር ተደራሽ በማድረግ ባደረጉት ንግግር በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት የአፍሪካ ወታደሮች ለፈረንሳይ " በግዳጅ እንዲሰማሩ ፣ ጥሩ በሆነ መንገድ እንዳይያዙ እና በመጨረሻም እንደተከዱ" አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ወታደሮች ባይኖሩ ፈረንሳይ ምንአልባት አሁን ድረስ በጀርመን ተይዛ ነበር በማለት ጠቅሰዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia