ተመድ ፤ ከ30 ሚሊዮን በላይ ሱዳናውያን ባልተጠበቀዉ ቀዉስ ምክነያት አስቸኳይ እርዳታ ይፈልጋሉተመድ እንዳሳወቀው 30.4 ሚሊዩን ሰዎች ፤ ብዙዎቹ ህፃናት ከሀያ ወራት ጦርነት በኋላ አስቸኳይ እርዳታ ይፈልጋሉ። ይህንን " ያልተጠበቀ ሰብአዊ ቀዉስ" መፍትሔ ለመስጠት ተመድ 4.2 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገኘል ብሏል ፤ 20.9 ሚሊዩን ሰዎቸን ለመርዳት እቅድ አድርጓል። በዚህ ግጭት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከስምንት ሚሊዩን በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ከዚህ ጦርነት በፊት የተፈናቀሉት ጨምሮ ሱዳን አሁን ላይ በአለም ከፍተኛ የተፈናቃዩች ቁጥር ያላት አንደኛ ሀገር ሆናለች። በተጨማሪም 3.3 ሚሊዩን ሰዎች ከሀገሪቱ ወጥተው ተሰደዋል ይህም ከጦርነት በፊተሰ የነበረውን የሱዳን ህዝብ ቁጥር አንድ አራተኛ ይሆናል።በአምስት ክልሎች ከፍተኛ ረሀብ የታወጀ ሲሆን አምስት ተጨማሪ ክልሎች እስከ ግንቦት እየተጠበቁ ነዉ ፤ 8.1 ሚሊዩን ሰዎች ለረሀብ ተጋልጠው ይገኛሉ።እነዚህ ሁኔታዎች በጣም አስፈላጊ በሆኑበት ሁኔታ ለችግር የተጋለጠውን ህዝብ ለመርዳት ተመድ የሚያስፈልገውን የእርዳታ ገንዘብ አንድ አራተኛ ለማግኘት እየታገለ ነዉ።ምስል ኦቻ / አላ ከሄርበእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia