ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ከካናዳው ገዥ ፓርቲ መሪነትታቸው እንደሚለቁ ሰኞ እለት ይፋ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ዘገባዎች ገለጹጀስቲን ትሩዶ ከገዢው የካናዳ ሊበራል ፓርቲ አመራርነት መልቀቃቸውን ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ፤ ይሁን እንጂ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ወዲያውኑ እንደሚለቁ ወይም አዲስ መሪ እስኪመረጥ ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንደሚቆዩ ገና ግልፅ አይደለም ሲል ዘ ግሎብ ኤንድ ሜይል ሶስት ስማቸው ያልተጠቀሱ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።የህትመቱ ምንጮች ትሩዶ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ መቼ እንደሚያሳውቁ ባያውቁም ረቡዕ ዕለት ከሚደረገው የፓርቲ ስብሰባ በፊት እንደሚሆን እርግጠኞች ናቸው። ሦስቱ ምንጮችም የሊበራል ፓርቲ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትሩዶን ለመተካት ምን ለማድረግ እንዳቀደ እርግጠኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።በአመራር ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን የሚወስነው የካናዳ ሊበራል ፓርቲ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በዚህ ሳምንት ለመገናኘት አቅዷል። ቀደም ሲል መገናኛ ብዙሃን ከ50 በላይ የሊበራል ፓርቲ ፓርላማ አባላት ትሩዶ ከስልጣናቸው እንዲለቁ በአንድ ድምፅ መወሰናቸውን ዘግበው ነበር። የካናዳው አዲስ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኤን ዲ ፒ) መሪ ጃግሚት ሲንግ ትሩዶ ከስልጣን እንዲለቁ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በቀጣዩ ፓርላማ ስብሰባ ላይ በካናዳው መሪ ላይ ድምጽ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia