የኢትዮጵያ አየር መንገድ "የአመቱ ዘላቂ ብራንድ" የሚል ሽልማት ከሲኤኤሲ የበረራ መፅሄት፤ በስካይ ትራቭል ሽልማት 2025 ላይ ተቀበለ አየርመንገዱ ይህንን ትልቅ የሆነ የእውቅና ሽልማቱ በአቬሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ እየሰጠ ያለውን ትጋት የተሞላበትን የላቀ አገልግሎት እንዲያስቀጥል የሚያደርገው መሆኑን በአፅንኦት አሳውቋል።ሲኤኤሲ የበረራ መፅሄት ፤ ከጎርጎሮሳውያኑ 1982 ጀምሮ በኢሲያ ሲታተም የቆ ታዋቂ የበረራ መፅሄት ነው ፤ አሸናፊዎቹ የተለዩት በአንባቢያን ምርጫ ፣ የባለሙያዎች ግምገማ እና በኢዲቶርያል ክለሳ ነው። በሳምንት 28 በረራዎችን ከአዲስ አበባ ወደ ቤጂንግ ፣ ሻንጋይ ፣ ጉዋንዙ እና ቼንግዱ የሚያደርገው የኢትዩጵያ አየር መንገድ አፍሪካን እና ቻይናን ድልድይ ሆኖ እያገናኘ ሲሆን ፤ የአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ ራሱን እያጠናከረ በአለምአቀፍ ደረጃ በአቬሽን መስክ ያለውን ተቀባይነት እያሳደገ ነው በማለት ፋና ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia