የኤም23 አማፂያን የዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ እስትራቴጂካዊ የብዙ ሚሊዮኖችን ከተማ የሆነችውን ጎማን ለመያዝ በር ከፋች የሆነችውን ማሲሲን ተቆጣጠሩየኤም23 አማፂያን በምስራቅ ኮንጎ የምትገኘውን የማሲሲ ግዛት አስተዳደር ዋና ከተማ ማሲሲን ተቆጣጠሩ ። 40,000 ሰዎች የሚኖሩባት ፣ በግብርና እና የማአድን ሀብቶቿ የምትታወቀው ማሲሲ ከከባድ ውጊያ በኋላ የመንግስት ወታደሮች እና አጋር ታጣቂዎች ከከተማዋ ካፈገፈጉ በኋላ ነው በማለት የአካባቢው ሚዲያዎች ዘግበዋል። በተመሳሳይ አካባቢ የምተገኘዉ የሉሼቤር ከተማ በቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ የማሲሲ መያዝ የአካባቢው ነዋሪዎች አማፂያኑ በደል ይፈፅሙብናል በሚል ፍራቻ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲፈናቀሉ አድርጓቸዋል። ብዙዎቹ ነዋሪዎች በሆስፒታሎች ፣ በቅርብ ባሉ ቦታዎች እና በአካባቢው ቤተክርስቲያኖች የተጠለሉ ሲሆን በሲቪል ዜጎች ላይም የደረሰ የመቁሰል አደጋም ተመዝግቧል።የኦካፒ ራዲዩ ጣቢያ አፅንኦት በመስጠት እንደዘገበዉ የማሲሲ መያዝ የኤም23 አማፂያን ባለቸው ኃይል የሰሜን ኪቩ ግዛት ዋና መቀመጫ ወደሆነችው ፤ የሁለት ሚሊዩን ነዋሪዎች መኖሪያ ወደሆነችው እና በ80 ኪሜ ላይ ወደምትገኘው ጎማ እየገሰገሱ ነው። የግዛቲቱ ምክትል አስተዳዳሪ አሌክስ ባሁንጋ ፤ ለምእራባውያን የዜና አውታር ሁኔታውን ሲያስረዱ " አሳሳቢ ሰብአዊ ቀዉስ" እንደሆነ እና የኮንጎ መንግስት የጦር ኃይሉን የውጊያ አቅም እንዲያጠናክር ጠይቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኤም23 አማፂያን በአካባቢው በሚገኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተሰብስበው ድርጊታቸው "ሀገሪቱን ነፃ ለማውጣት" ያሰበ እንደሆነ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia