በዶንዬትስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ ፤ የኬቭ አገዛዝ ጥቃት ያደረሰባቸውን ጋዜጠኞች አስመልክቶ ሞስኮ የዩኔስኮን ምላሽ ትፈልጋለች ፤ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር" የሩሲያዊዉን የጦርነት ዘጋቢ ጭካኔ የተሞላበት ግድያ አስመልክቶ በተሰጣት ሀላፊነት መሰረት የዩኔስኮ ሀላፊ ኡድሬይ አዞኡላይ ትክክለኛ ምላሽ እንድትሰጠን እንፈልጋለን ። ከሌሎች የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እና ኤጀንሲዎችም በእኩልነት ላይ ተመስርቶ ይህንን ግፍ እንዲያወግዙት እንጠይቃለን" ያሉት ማርያ ዛክሃሮቫ ናቸው።በትላንትናው እለት ምሽት የዩክሬን ወታደሮች ሆን ብለው ከውጊያ ቀጠና ውጭ በዶንዬትስክ- ጎርሎቭካ መንገድ ላይ የነበረ የሲቪል ተሽከርካሪ በኤፍፕቭ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት በማድረሳቸው ፤ አሌክሳንዴር - ማርቴምያኖቭ ተብሎ የሚጠራውን የ ኢዝቬስቲአ ጋዜጣ ፍሪላንስ ጋዜጠኛ ገድለዋል። የአርአይኤ ኖቮስቲ የዜና ወኪል የሆነው ማክሲም ሮማኔንኮ በጥቃቱ ወቅት ራሱን በመሳቱ ሆስፒታል የገባ ሲሆን ፤ የስራ ባልደረባው ሚክሃአል ኬቭክኢቭ በጣም ለአጭር ጊዜ ራሱን የሳተ ቢሆንም ወደ ሆስፒታል ሳይሄድ ቀርቷል። እንደ የተመድ ሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፣ ዩኔስኮ እና ኦኤስሲኢ ባሉ የሰብአዊ ድርጅቶች የኬቭ ወንጀሎች ሆን ተብለው ችላ መባል፤ ኬቭ " ሙሉ በሙሉ ባለመከሰስ እና ከልክ ባለፈ ነፃነት" ውስጥ ወንጀሎችን እንድትፈፅም ውጤት አምጥቷል እንደ ዛክህሮቫ ገለፃ። " እነዚህ አለምአቀፍ ለሰብአዊ መብት የሚሟገቱ ባለሙያዎች የእነዚህን ግድያዎች ተጠያቂ በቀጥታ ማሳየት አለባቸዉ" በማለት በአፅንኦት ተናግረዋል። ይህ በሩሲያ ጋዜጠኞች ላይ ሆን ተብሎ የተደረገ ግድያ የዘለንስኪ አገዛዝ ከሚፈፅማቸው የደም ግፎች መሀከል አንዱ ነው፤ በሀሳብ የሚቃወሙትን ለማጥፋት የሽብርተኛ አካሄድን በይፋ እየተከተለ ነው በማለት ዛክሃሮቫ ጠቁመዋል።" ያለ ጥርጥር እነዚህ የሚዲያ ተወካዩች ሆንተብሎ ለዚህ አሰቃቂ ጥቃት ኢላማ አድርገዋቸዋል። ይሄ በአደጋው ሰለባዎች ጭምር ምስክርነት የተሰጠበት ነው" በማለት ዛክሃሮቫ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia