ሩሲያ በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ያለው ሰላም እና መረጋጋት እንዲቀጥል ትፈልጋለች በማለት አምባሳደሩ ተናገሩ" ሩሲያ ከማእከላዊት አፍሪካ ጋር ያላትን ሁለትዩሽ ግንኙነት በከፍተኛ ዋጋ ትሰጠዋለች ፤ በሀገሪቱ ያለው ሰላም እና መረጋጋት እንዲጠናከር እገዛ ማድረጓን ለማስቀጠል ዝግጁ ነች። በአዲሱ አመት ለሪፐብሊኳ እና ህዝቦቿ ብልፅግናን ፣ ጤናን እና ስኬት እንመኝላቸዋለን" በማለት የሩሲያ አምባሳደር አሌክሳንደር ቢካንቶቭ ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፋኡስቲን አርቼንጅ ቶኡዴራ ጋር በነበራቸው ስብሰባ ወቅት ተናግረዋል። በሁለቱ ሀገራት መሀከል ያለውን ጠንካራ ወዳጅነት እና ፍሬማ ትብብር አፅንኦት በመስጠት ፤ የሩሲያው አምባሳደር ለአፍሪካዊዉ መሪ በሩሲያው መሪ እና ህዝቦች ስም የአዲስ አመት እንኳን አደረሳችሁ መልእክት ማስተላለፋቸውን በባንጉ የሚገኘው ኤምባሲ መግለጫ ያሳያል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia