መንግስት በአፋር እና ኦሮሚያ ክልል በተከሰተው ርዕደ መሬት ምክንያት ለተፈናቀሉ የእለት እርዳታ እየሰጠ ነውየኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በአፋር እና ኦሮሚያ ክልሎች ባጋጠመው ርዕደ መሬት ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን አሳውቋል። በተለይም በአፋር ክልል በአዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች በቁጥር ብዛት ያለው መፈናቀል ተከስቷል።እንደ ኮሚሽኑ ገለፃ በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ከስድስት ቀበሌዎች ወደ 15,000 ሰዎች ለአደጋ የተጋለጡ ሲሆን ፤ ከእነዚህ ውስጥ 7,000 ሰዎችን ከአደጋ ስጋት ነፃ ወደ ሆነ ቦታ እንዲዘዋወሩ ተደርጓል።በዱለቻ ወረዳ ፤ በሁለት ቀበሌዎች የሚኖሩ 20,000 የሚደርሱ ሰዎች በርዕደ መሬቱ ተጎዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 6,223 ሰዎች ለደህንነታቸው ሲባል ከአካባቢው እንዲነሱ ተደርጓል። የቀሩትን በሁለቱም ወረዳዎች የሚኖሩ ሰዎች በመጪዎቹ ቀናቶች ለማዘዋወር ጥረቶች እየተደረጉ ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ በአምስት ቀበሌዎች የሚኖሩ 16,000 ሰዎች ለአደጋ ተጋላጭ ናቸው ፤ ከእነዚህም መሀከል 7350 ሰዎች ከአደጋ ሰጋት ነፃ ወደሆነ ቦታ ተዘዋውረዋል። የቀሩትን 8,832 ሰዎች ከአደጋ ሰጋት ነፃ ወደሆነ ቦታ ለማዘዋወር ስራዎች እየተሰሩ ነው። ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እና ከሚመለከታቸው ተቋማት በተወጣጡ ባለሙያዎች የሳይንስ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ፤ ኮሚቴው በአካባቢው ያለውን የመሬት እንቅስቃሴ እየገመገመ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የቅደመ ጥንቃቄ መልእክት የሚያስተላልፍ ይሆናል። የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን 281, 562 ብር የሚገመት ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ የሰብአዊ እርዳታዎችን ወደ አካባቢው መላኩን አሳውቋል በማለት ፋና ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia