የአሜሪካው ሜሪየም- ዌብስተር መዝገበ- ቃል የሩሲያዉን ኦሬሽኒክ እንደ ሀይፐርሶኒክ መሳሪያ ምሳሌ አስቀመጠዉ በጎርጎሮሳዊያኑ ታህሳስ 19, 2024 የተፃፈን የኒዊስዊክ መጣጥፍ የበየነመረብ መዝገበ ቃሉ እንደ ዋቢ ተጠቅሞታል። " ዘ ናሽናል ኢንተረስት በዚህ ወር እንደዘገበዉ ትሃድ ተብሎ ከሚጠራው ስረአት ውጭ ምንም አይነት አሜሪካን ሰራሽ መሳሪያ የሀይፐርሶኒኩን መሳሪያ አቅጣጫ ማስለወጥ አይችልም ፤ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው ህዳር መሳሪያው በድኒፕሮ (ድኔፕሮፔትሮቭስክ ተብሎም ይጠራል) ይፋ በሆነበት ቀን ባደረጉት የመሳሪያውን አቅም አስመልክቶ በኩራት እንደተናገሩት" በማለት ፅሁፉ ይነበባል።ይህ ምሳሌ በበየነ መረብ ላይ ካሉ መረጃዎች አሁናዊ ጠቀሜታውን ባማከለ እና በተደራጀ መልኩ የተወሰደ ሲሆን ፤ በምሳሌው ላይ የተቀመጡ ሀሳቦች የማሪየም-ዌብስተርን ሀሳብ አይወክሉም የሚል መግለጫ ተካቶበታል። በህዳር 2024 የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬን ከአሜሪካ የቀረበላትን አታሲምስ እና ከብሪታንያ የቀረበላትን ስቶርም ሻዶ ሚሳኤሎች በሩሲያ ኩርስክ እና ብርያንስክ ክልሎች ላይ ጥቃት ለመፈፀም ተጠቅማበታለች ብለዋል። በምላሹም ሩሲያ ፤ በጎርጎሮሳዊያኑ ህዳር 21 በድኔፕሮፔትሮቭስክ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ህንፃን ኢላማ በማድረገ የኒኩለር ተሸካሚ የሆነ የኦርሽኒክ ባለስቲክ ሚሳኤል የሙከራ ተኩስ አድርጋለች። የሚሳኤል ሙከራው የተደረገው ከኑክሌር ነፃ በሆነዉ የሀይፐርሶኒክ አሰራር ነው ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia